ሁለተኛው ዙር የጣና ቤተሰብ ስኮላርሺፕ አሸናፊ ተማሪዎች ታወቁ

ሁለተኛው ዙር የጣና ቤተሰብ ስኮላርሺፕ አሸናፊ ተማሪዎች
ተለይተዋል

ለሁለተኛው ዙር የጣና ቤተሰብ ስኮላርሺፕ ስኬታማ እንዲሆን በመቆም ላበረታታችሁን፤ ቃላችንን አምናችሁ ገንዛባችሁንና ጊዜአችሁን ሳትሳሱ ለደገፋችሁን የከበረ አክብሮታችን ይድረሳችሁ። ጣናሃይቅ ት.ቤት ባትማሩም በሃሳባችን ተስማምታችሁ ድጋፍ ላደረጋችሁልን በሙሉ እጅግ በጣም እናመሰግናለን። የገንዘብ የማሰባሰብ ዘመቻው ጥቅምት 30,2011 (November 9,2018) ይጠጥናቀቃል::

ባለፈው ዓመት በሁላችሁም ስጦታ የመጀመሪያው ዙር ስኮላርሺፕ በልዩ ሁኔታ ተሳክቷል:: 24 ተማሪዎችን በየወሩ በወጪ ደግፈናል: ለ100 ሴት እህቶቻችን ንፅህና መጠበቂያ በየወሩ አቅርበናል: ለ2 ዓይነስውራን ወንድሞቻችን ለትምህርታቸው የሚረዳ ዘመናዊ የድምፅ መቅጃ ገዝተን ልከናል: የት/ቤቱን ቤተ-መጻህፍት ካለበት የመጽሃፍ ዕጥረት ለመታደግ “አንድ መጽሃፍ ለአንድ ተማሪ” በሚል የድጋፍ ዘመቻ ከ620 በላይ መጻህፍት (reference books) ለትምህርት ቤቱ ለግሰናል::

ትቤቱንና ተማሪዎችን ለመደገፍ የሚሰሩ ሌሎች ስራዎንን ለመደገፍ ከእኛ ጋር እንደምትሰሩ በሙሉ ልባችን እንተማመናለን። ቀና ተሳትፏችሁን በቋሚነት ለመቀጠል በድረገፃችን ላይ የሚገኘውን የአባልነት ፎርም እንድትሞሉም እንጋብዛለን(https://tanahaikbdr.com/contacts/)

ድር ቢያብር ነውና ብሂሉ የሁሉም ሰው ተሳትፎ ለስኬት ያበቃናል:: በህብረት ለታናናሾቻችን የተሻለ ነገን እናውርስ::በጋራ ዓላማችን እንደምናሳካ እርግጠኞች ነን!

ሁለተኛው ዙር የጣና ቤተሰብ ስኮላርሺፕ አሸናፊ ተማሪዎች
10ኛ ክፍል :
  • መላከሰላም ገዳሙ
  • ኪዳነማርያም ዉበቴ
  • እህተሙሴ ነብዩ
  • አበቡ ዉበቴ
  • ጸደይ አበበ
  • ፍቅርአዲስ አስቻለ
11ኛ ክፍል:
  • ገሊላ ብዙአየሁ
  • ዳዊት አዳሙ
  • በረከት አዳሙ
  • ዳኛቸዉ ተሰማ
  • ብርሃነመስቀል ወርቁ
  • ፍቅሩ ውቤ
12ኛ ክፍል:
  • ያብስራ ፍቃዴ
  • ሜሮን ማዘንጊያ
  • አበበ ወሌ
  • ዮናስ አበበ
  • ሙላት ጌጡ
  • አምሳሉ አሞኝ
If any of you reading this would love to continue your support, please use the link below.
ኢትዮጵያ ውስጥ ያላችሁ ቀጥታ ዳሽን ባንክ በሚከተለው የባንክ አካውንት ማስገባት ትችላላችሁ፤
ዳሽን ባንክ ባህርዳር ቅርንጫፍ
የባንክ አካውንት ቁጥር፤ 5020904670002
Swift Code = DASHETAA
OR
Please invite more friends to join THAN viber group –
ይህ ቪዲዮ የተሰሩ ስራዎችን ባጭሩ ያሳያል
ከአክብሮት ጋር እናመሰግናለን።
የህብረቱ አስተባባሪዎች

2010 TFS WINNERS

1 thought on “ሁለተኛው ዙር የጣና ቤተሰብ ስኮላርሺፕ አሸናፊ ተማሪዎች ታወቁ

  1. Pingback: የ2011 የ9ኛ ክፍል የጣና ቤተሰብ ስኮላርሺፕ አሸናፊ ተማሪዎች ታወቁ | የጣና ሐይቅ ምሩቃን ቤት

comment