የ9ኛው ዙር የጣና ቤተሰብ ስኮላርሺፕ አሸናፊ ተማሪዎች

10ኛ ክፍል የጣና ቤተሰብ ስኮላርሺፕ አሸናፊ ተማሪዎች

11ኛ ክፍል የጣና ቤተሰብ ስኮላርሺፕ አሸናፊ ተማሪዎች

12ኛ ክፍል የጣና ቤተሰብ ስኮላርሺፕ አሸናፊ ተማሪዎች

1ኛ ዓመት ዩኒቨርሲቲ የሚገቡ

የቴክኖሎጂና ሮቦቲክስ ስልጠና ለተማሪዎች ተሰጠ

በጣና ሐይቅ አጠቃላይ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት የሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ክበብ አስተባባሪነት ባለፉት 2 ወራት ሲሰጥ የቆየው የሮቦቲክስ እና ቴክኖሎጂ ስልጠና ከ 40 በላይ የሚሆኑ የ9ኛ፣10ኛ፣ 11ኛ እና 12ኛ ክፍል ተማሪዎችን በማሰልጠን የምርቃት ስነስርዓት በማካሄድ መጋቢት 18 , 2018 ዓ/ም ተጠናቋል፡፡

በዚህም ፕሮግራም ከሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ቢሮ አቶ ሀብታሙ ስሜነህ ፣ ከባህር ዳር ዩኒቨርስቲ አቶ አዱኛ ነጮ ፣ የቀድሞ የትምህርት ቤቱ ርዕሰ መምህር አቶ ሙጬ ባዘዘው ፣ የትምህርት ቤቱ መምህራን እና የአስተዳደር ሰራተኞች እና ተማሪዎች ተገኝተው በተማሪዎች የተሰሩ ፕሮጀክቶችን በመጎብኘት ተማሪዎቹን አበረታትተዋል።

ተመራቂ ተማሪወች Smart Agriculture , AI Assisted Robot, Home Automation, Radar Control System,  Digital Meter, Home Security እና ሌሎች ፕሮጀክቶችን በመስራት ለእይታ አቅርበዋል። የሳይንስና ቴክኖሎጂ ክበብ አስተባባሪ ወ/ሮ ፋሲካ ሞላ ሀሳቡን በመጀመር እና ከሚመለከታቸው የትምህርት ቤቱ አመራር ጋር በመሆን ይሄ ስልጠና እንዲሳካ አድርገዋል፡፡ በዚህ ስልጠና ትምህርት ቤቱ ለፕሮጀክቶቹ የእቃ ግዥ እና ምቹ  ማስተማሪያ ክፍል በማዘጋጀት ድጋፍ አድርጓል። ተማሪዎችን በማስተማር የቀድሞ ተማሪዎች ሕብረት አስተባባሪ እና የባህርዳር ዩንቨርሲቲ መምህር አቶ ተናኘ ፍቅሬ የበጎ ፈቃደኝነት ስልጠና ሰጥተዋል ። ለዚህ ፕሮግራም ማስኬጃ ይሆን ዘንድ አቢሲኒያ ባንክ ድጋፍ አድርጓል። የተሳተፉትን ሁሉ እናመሰግናለን፡፡

የጣና ሐይቅ የቀድሞ ተማሪዎች ሕብረት