የ5ተኛው ዙር የጣና ቤተሰብ ስኮላርሽፕ አሸናፊ ተማሪዎች ታወቁ

የጣና ሐይቅ የቀድሞ ተማሪዎች ህብረት የ2014 ዓ.ም ዕቅድ መሰረት የሚከተሉትን ስራዎች አጠናቁዋል :-

  1. የ5ተኛው ዙር የጣና ቤተሰብ ስኮላርሽፕ 32 አሸናፊ ተማሪዎችን በመለየት ሸልሟል፣
  2. ለ261 ሴት ተማሪዎች ንጽህና መጠበቂያ (Sanitary Pads) የመግዛት አቅም ለሌላቸው እገዛ አድርጓል፣
  3. ለ5 ዓይነ ስዉራን ተማሪዎች ለትምህርታቸው የሚረዳ የድምፅ መቅጃ መሳሪያ አቅርቧል፣
  4. ከ105 ሺህ ብር በላይ ወጪ በማድረግ 5,000 ሊትር የሚይዝ የውሃ ማጠራቀሚያ (water tank) በመግዛት እንዲሁም የትምህርት ቤቱን የቧንቧ መስመር አሰርቶ ለአገልግሎት አብቅቷል::

ለሥራው መሳካት የተባበሩትን በሙሉ ከልብ እናመሰግናለን::

ት/ቤቱን እና ተማሪዎችን ለመደገፍ እንዲሁም የሚሰሩ ሌሎች ስራዎችን ለመደገፍ ከእኛ ጋር እንደምትሰሩ በሙሉ ልባችን እንተማመናለን። ቀና ተሳትፏችሁን በቋሚነት ለመቀጠል በድረገፃችን ላይ የሚገኘውን የአባልነት ፎርም እንድትሞሉም እንጋብዛለን(https://tanahaikbdr.com/contacts/)

YouTube/Facebook: Tana Haik Alumni Network

Twitter: @HaikTana

በህብረት ለታናናሾቻችን የተሻለ ነገን እናውርስ!

የጣና ሐይቅ የቀድሞ ተማሪዎች ሕብረት

ታህሳስ 2014 ዓ.ም