የ7ኛው ዙር የጣና ቤተሰብ ስኮላርሺፕ አሸናፊ ተማሪዎች ታወቁ

የጣና ቤተሰብ ስኮላርሺፕ (Tana Family Scholarship-TFS) ፣ በጣና ሐይቅ የቀድሞ ተማሪዎች ህብረት (Tana haik Alumni Network-THAN) እና በበጎ አድራጊዎች የገንዘብ ድጋፍ አማካኝነት፣ በየዓመቱ  በክፍል ውጤታቸውና በቤተሰብ ገቢ ሁኔታቸው የተመረጡ የ10ኛ፣ 11ኛ፣12ኛና ወደ ዩኒቨርስቲ መግቢያ ያገኙ 1ኛ ዓመት ታዳጊ የጣና ሃይቅ ትምህርት ቤት ተማሪዎችን ውጤታማ እንዲሆኑ የሚያግዝ ፕሮግራም ነው:: 

በዚህ መሰረት፣ በዚህ ዓመትም የጣና ሐይቅ የቀድሞ ተማሪዎች ኅብረት ባወጣው መስፈርት መሰረት 7ኛው ዙር የጣና ቤተሰብ ስኮላርሺፕ አሸናፊ 32 ተማሪዎች ተመርጠዋል፡፡

የአሸናፊዎች ዝርዝርም በክፍል በክፍል እንደሚከተልው ቀርቧል። 

10ኛ ክፍል

  1. ተመስገን አማረ
  2. ሃና አዳነ
  3. ፋሲካ ሙሉ
  4. ነሲቡ በላይነህ
  5. አስፋው በቀለ
  6. ደመቀች ዋሴ
  7. ቤተልሄም ጋሻው
  8. ማሩ አለማንተ

11ኛ ክፍል

  1. ፍቅርተማርያም ታምሩ
  2. መቅደስ በላይነህ
  3. ሮዛ ጓዴ
  4. ፍሬገነት በቀለ
  5. ፍቃዱ ቤዛ
  6. ዳዊት ማሃባው
  7. ኤደን ገ/ሂወት
  8. ይትባረክ መልካሙ

12ኛ ክፍል

  1. አገር አምላክ
  2. መዝገቡ ውበት
  3. በሪሁን ምትኬ
  4. ቅድስት ማሩ
  5. አእምሮ ታደሰ
  6. ስማኮነ መላክ
  7. ስመኘው አጉማስ
  8. ልቦና እንደሻው

1ኛ ዓመት ኮሌጅ የሚገቡ

  1. ሃይለማሪያም ሉሉ
  2. ሙሉቀን ተሻገር
  3. ምንታምር በለጠ
  4. ፈንታሁን ሞላ
  5. መስፍን አስፋው
  6. መርድያ በለጠ
  7. መላከሰላም ላዋየው
  8. ኢዮብ መለሰ

ይህ ድጋፍ እንዲሳካ በብዙ የደከማችሁ፣ የህብረቱ አባላትና አመራሮች፣ በጎ አድራጊዎች፣ የት/ቤቱ እመራሮችና የባህር ዳር አስተባባሪዎችን በሙሉ ከልብ እናመሰግናለን::  

ቀና ተሳትፏችሁን በቋሚነት ለመቀጠል በድረገፃችን ላይ የሚገኘውን የአባልነት ፎርም እንድትሞሉም እንጋብዛለን https://tanahaikbdr.com/contacts/

አድራሻዎቻችን፦

ስለህብረቱና ስለሚሰራቸው ስራዎች ይበልጥ ለማወቅ የሚከተለውን ብሮሸር መመልከት ይቻላል።

የ2015 6ኛው ዙር አሸናፊዎች ፎቶዎች

በህብረት ለታናናሾቻችን የተሻለ ነገን እናውርስ!

የህብረቱ አስተባባሪዎች

7ተኛው ዙር የጣና ቤተሰብ ስኮላርሺፕ – ኑ ትውልድ እናፍራ!

https://www.gofundme.com/f/tfs-7th-round

የጣና ቤተሰብ ስኮላርሺፕ በላቀ የትምህርት ውጤታቸውና በቤተሰብ ገቢ ሁኔታቸው የተመረጡ ታዳጊ ተማሪዎችን ውጤታማ እንዲሆኑ የሚያግዝ፣ ሴት ተማሪዎችን በልዩ ሁኔታ የሚያበረታታና ለአካል ጉዳተኛ ተማሪዎችም እገዛ የሚያደርግ ፕሮግራም ነው።

እስካሁን ለስድስት ዓመታት ባካሄዳቸው 6 ዙሮች :-

  • ከ170 በላይ ተማሪዎችን በየወሩ በወጪ ደግፏል፣
  • ከ1000 በላይ ለሆኑ ሴት ተማሪዎች ወርሃዊ ንጽህና መጠበቂያ በየወሩ አቅርቧል፣
  • ለዓይነስውራን ተማሪዎች የሚያግዙ ድምፅ መቅጃዎችን አቅርቧል፣
  • ወደ ዩንቨርሲቲ ለሚገቡ ተማሪዎች የዝግጅት ወጪን ሸፍኗል፣
  • የኮምፒውተር ላብራቶሪዎችን የኔትወርክና ኤሌክትሪክ ዝርጋታ በባለሙያ አሰርቷል ፣
  • የሴት ተማሪዎች መፀዳጃ ቤት አሳድሷል ፣
  • እንዲሁም የመምህራን ማረፊያ ክፍል እድሳት እና አዲስ ሎከሮችን አሰርቷል፣

በተጨማሪም የግቢው አጠቃላይ የኤሌክትሪክ ዝርጋታ የማስተካካያ አሰርቷል፣ የመጽሐፍ ማሰባሰብ ዘመቻዎች አድርጓል፣የቤተመጽሐፍት ወንበሮች ድጋፍና የመጠጥ ውሃ ማጠራቀሚያ (water tank) ለግሷል፣ የፅዳት ዘመቻዎች አካሂዷል።

ሁሉም ሥራዎች የተሳኩት ግን ይህን በጎ ዓላማ ሰምተው በደገፉ ብዙ የተባበሩ እጆች ነው!!

ባለፉት ዙሮች በነበረው ተሳትፎ ከቀድሞ ተማሪዎች በተጨማሪ ሁሉም በጎ አሳቢ ኢትዮጵያውያንና፣

ጉዳዩን ከወዳጆቻቸው የሰሙ የውጭ ሀገር ዜጎችም ጭምር መሳተፋቸውን አይተናል። በመጪው የ2016 የትምህርት ዓመትም የቀድሞ ተማሪዎች ሕብረት ይህን በጎ ሥራ ለማስቀጠል ከዚህ በታች ያለውን ዕቅድ አውጥቶ በየዓመቱ የሚያደርገውን የገቢ ማሰባሰቢያ መርሃ ግብር ጀምሯል። እርስዎም ይሳተፉ ለወዳጆችዎም ያጋሩ!!

በዚህ ለ7ተኛ ጊዜ በሚደረገው “የጣና ቤተሰብ ስኮላርሽፕ” ድጋፍ የሚከተሉትን 6 ዕቅዶች ለማከናወን ታስቧል፦

የጣና ሐይቅ የቀድሞ ተማሪዎች ህብረት- የ2016 ዓ.ም ዕቅድ

  • 1. በትምህርት ውጤትና በቤተሰብ ገቢ ሁኔታ የተመረጡ 32 ተማሪዎችን ለአንድ ዓመት በወጪ ማገዝ ከመስከረም – ሰኔ ለእያንዳንዳቸው 1000 ብር (10 ወር * 32 ተማሪዎች * 1000 ብር) – 320,000 ብር
  • 2. ለ 250 እገዛ ለሚያስፈልጋቸው ሴት ተማሪዎች የንጽህና መጠበቂያ (Sanitary Pads) ለአንድ ዓመት ማቅረብ 150,000 ብር
  • 3. ሴት ተማሪዎች በወር አበባ ጊዜ ድንገተኛ ህመም ሲያጋጥም የእረፍት መውሰጃ እና መታጠቢያ ክፍል ለማሳደስ 66,200 ብር
  • 4. ለ5 ዓይነ ስዉራን ተማሪዎች ለትምህርታቸው የሚረዳ የድምፅ መቅጃ መሳሪያ መግዛት 20,000 ብር
  • 5. ወደ ዩኒቨርሲቲ ተመድበው ለሚገቡ እገዛ ለሚያስፈልጋቸው ተማሪዎች ድጋፍ ማድረግ እና የጣና ቤተሰብ ስኮላርሺፕ ተማሪዎች ህክምና መጠባበቂያ በጀት 70,000 ብር
  • 6. የህብረቱን ስራዎች ባህር ዳር ላይ ለሚሰራ ጸሐፊ የዓመት ደሞዝ ከመስከረም እስከ ነሐሴ 5000*12ወር= 60,000 ብር

በድምሩ 686,200 ብር የሚገመት ወጪ በማድረግ እነዚህን ሥራዎች ለማሳካት ታቅዷል፡፡ እስካሁን ባለፉት 6 ዙሮች የነበረው የተማሪዎች እገዛ የተሳካው ይህን በጎ ሥራ የሰሙና የወደዱ ሁሉ ባደረጉት ያላሰለሰ የገንዘብ ፣ የሃሳብ እንዲሁም የጉልበት ድጋፍ ነው፡፡ በመሆኑም 7ተኛውን ዙር በተሻለ ሁኔታ ለማሳካት ጥሪ ስናቀርብ ድጋፋችሁ እንደማይለየን በመተማመን ነው።

7th round TFS Gofundme

ኢትዮጵያ ውስጥ ያላችሁ በቀጥታ በሚከተሉት የሕብረቱ የጋራ የባንክ አካውንቶች ማስገባት ትችላላችሁ፤

– የንግድ ባንክ አካውንት ቁጥር፤ 1000408845622

– የዳሽን ባንክ አካውንት ቁጥር፤ 5020904670002

Dashen Bank Swift Code = DASHETAA

================

About Tana Haik Alumni Network

In the year 2012, a few former-students who lived in Ethiopia and abroad volunteered to work together for the cause of giving back to their school, Tana Haik and the community. They established the alumni group with a vision: “Together, we can make a difference to bring a bright future for students in our community!”. It was launched by supporting the school through providing furniture and Internet service to the Library, and organizing donation of books. In just a few years, alumni from all over the world shared the vision and expanded dimension of the support to students and the school. Currently, there are alumni members from various batches and volunteers participating in annual fundraisers and campaigns to support current students.

~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~

ስለ ጣና ሐይቅ የቀድሞ ተማሪዎች ሕብረት አጀማማር

የጣና ሐይቅ የተማሪዎች ሕብረት በኢትዮጵያና በውጭ ሀገር በሚኖሩ በጎ ፈቃደኛ የቀድሞ ተማሪዎች በ2014ዓም የተጀመረ ነው፡፡ ይዞም የተነሳው መርህ “በጋራ ስንሆን ለውጥ እናመጣለን፣ የተማሪዎችን የተሻለ የወደፊት መንገድም እንቀርፃለን” የሚል ነው፡፡ እገዛውን ሲጀምር የቀድሞ ተማሪዎችን በማሰባሰብ ለታዳጊ ተማሪዎች ሽልማት ሰጥቷል፣ መጽሃፍትን በመግዛት በስጦታ አበርክቷል፣ ትምህርት ቤቱ የኢንተርኔት አገልግሎት ተጠቃሚ እንዲሆን አድርጓል፡፡ እንዲሁም በአሁኑ ሰዓት ሕብረቱ ሰፍቶ በተለያዩ የትምህርት ዓመታት የጨረሱ፣በተለያዩ የዓለማችን ክፍሎች የሚኖሩ የቀድሞ ተማሪዎችን እና ዓላማውን የሚደግፉ በጎ ፈቃደኞችን አቅፎ በጋራ በመስራት ላይ ይገኛል፡፡

የሕብረቱ ዓበይት ዓላማዎች ፡-

  • ለተማሪዎች የገንዘብ እገዛ ማድረግ

የትምህርት ውጤትንና የቤተሰብ ገቢ ሁኔታን በመመዘን በየዓመቱ ለተመረጡ 32 ተማሪዎች ወርሃዊ የገንዘብ ድጋፍ ያደርጋል፡፡

በዚህም ተማሪዎቹ የሚኖርባቸውን የኑሮ ጫና በማቃለል ሙሉ ትኩረታቸውን ትምህርታቸው ላይ አድርገው የበለጠ ውጤታማ እንዲሆኑ ያግዛል፡፡

  • ለሴት ተማሪዎች ወርሃዊ የንጽህና መጠባቂያ ሞዴስ ማቅረብ

እገዛ የሚፈልጉ ሴት ተማሪዎችን በየዓመቱ በመመዝገብ 250 ለሚደርሱ ተማሪዎች በየወሩ የንጽህና መጠበቂያ ሞዴስ በትምህርት ቤት ውስጥ ያቀርባል፡፡

በዚህ ልዩ እገዛ ሴት ተማሪዎች በነፃነት ትምህርታቸውን እንዲከታተሉ ያግዛል፡፡

በተጨማሪም ለአስቸኳይ ጊዜ የሚሆን ሞዴስ ማንኛውም ሴት ተማሪ፣ መምህራን እና የግቢው ሴት ሰራተኞች እንዲገለገሉ በማሰብ በመጠባበቂያነት ጥቅም ላይ ውሏል፡፡

  • ለአካል ጉዳተኛ ተማሪዎች ልዩ እገዛ ማድረግ

ለዓይነስውራን ተማሪዎች በየዓመቱ ትምህርታቸውን ለመከታተል የሚረዳቸው የድምፅ መቅጃ መሳሪያ ያቀርባል፡፡

በቀጣይም ሌሎች ልዩ ድጋፍ የሚሹ አካል ጉዳተኛ ተማሪዎችን የማገዝ ዓላማ አለው፡፡

  • ለጣና ሐይቅ ት/ቤት የመሠረተ ልማት ሥራዎች ድጋፍ ማድረግ

ሕብረቱ ከዚህ በፊት የመጠጥ ውሃ ማጠራቀሚያ ገዝቶ ለትምህርት ቤቱ አቅርቧል፣ ለትምህርት ቤቱ ቤተመፅሐፍት መጽሐፍት የማሰባሰብ ዘመቻ አድርጓል ወንበሮች ለግሷል፣ በትምህርት ቤቱ ውስጥ የፅዳት ዘመቻዎችን አስተባብሯል፡፡

====================================================

የዚህ የቀድሞ የጣና ሐይቅ ተማሪዎች ሕብረት አስተባባሪዎች ነዋሪነታቸው በኢትዮጵያ፣በአሜሪካ እንዲሁም በአውሮፓ ሲሆኑ ስማቸው እንደሚከተለው ሰፍሯል፡፡

This scholarship is organized by the following former students and volunteers of Tana Haik

  • Solomon Nurga – Atlanta, USA
  • Dejenie Tarekegn – Maryland, USA
  • Tenager Bekalu – Helsinki, Finland
  • Geta Mehariw –Portland, USA
  • Solomon Kibret – California, USA
  • Meseret Ejigu – Bahir Dar, Ethiopia
  • Sileshi Minayehu – Bahir Dar, Ethiopia
  • Behailu Yirga – Bahir Dar, Ethiopia
  • Mastewal Alemu – Bahir Dar, Ethiopia
  • Eden Metaferia – Stockholm, Sweden
  • Bekalu Metalign – Addis Ababa, Ethiopia
  • Rahel Wondie – Addis Ababa, Ethiopia
  • Minwyelet Getinet – Grande Prairie, Canada
  • Lake Endalew – Virginia , USA
  • Tewodros Tesera – Maryland, USA
  • Yonatan Gossaye – London, UK
  • Misganaw Birhan – Turku, Finland
  • Henok Hailemariam– Maryland, USA

Tana Haik Alumni Network