8ተኛው ዙር የጣና ቤተሰብ ስኮላርሺፕ ገቢ ማሰባሰቢያ ተጀምሯል

የጣና ቤተሰብ ስኮላርሺፕ በላቀ የትምህርት ውጤታቸውና በቤተሰብ ገቢ ሁኔታቸው የተመረጡ ታዳጊ ተማሪዎችን ውጤታማ እንዲሆኑ የሚያግዝ፣ ሴት ተማሪዎችን በልዩ ሁኔታ የሚያበረታታና ለአካል ጉዳተኛ ተማሪዎችም እገዛ የሚያደርግ ፕሮግራም ነው።

እስካሁን ለሰባት ዓመታት ባካሄዳቸው 7 ዙሮች ከ $46,600 ዶላር በላይ በማሰባሰብ :-

ከ200 በላይ ተማሪዎችን በየወሩ በወጪ ደግፏል፣

ከ1300 በላይ ለሆኑ ሴት ተማሪዎች ወርሃዊ ንጽህና መጠበቂያ በየወሩ አቅርቧል፣

ከ35 በላይ ዓይነስውራን ተማሪዎች የሚያግዙ ድምፅ መቅጃዎችን አቅርቧል፣

ወደ ዩንቨርሲቲ ለሚገቡ ተማሪዎች የዝግጅት ወጪን ሸፍኗል፣

የኮምፒውተር ላብራቶሪዎችን የኔትወርክና ኤሌክትሪክ ዝርጋታ በባለሙያ አሰርቷል ፣

የሴት ተማሪዎች መፀዳጃ ቤት ስራ የገንዘብና የማማከር ድጋፍ አድርጓል

እንዲሁም የመምህራን ማረፊያ ክፍል እድሳት እና አዲስ ሎከሮችን አሰርቷል፣

• በተጨማሪም የግቢው አጠቃላይ የኤሌክትሪክ ዝርጋታ የማስተካካያ ስራ አሰርቷል፣ የመጽሐፍ ማሰባሰብ ዘመቻዎች አድርጓል፣የቤተመጽሐፍት ወንበሮች ድጋፍና የመጠጥ ውሃ ማጠራቀሚያ (water tank) ለግሷል፣ የፅዳት ዘመቻዎች አካሂዷል።

ሁሉም ሥራዎች የተሳኩት ግን ይህን በጎ ዓላማ ሰምተው በደገፉ ብዙ የተባበሩ እጆች ነው!!

ባለፉት ዙሮች በነበረው ተሳትፎ ከቀድሞ ተማሪዎች በተጨማሪ ሁሉም በጎ አሳቢ ኢትዮጵያውያንና፣ ጉዳዩን ከወዳጆቻቸው የሰሙ የውጭ ሀገር ዜጎችም ጭምር መሳተፋቸውን አይተናል። በመጪው የ2017 ዓ/ም የትምህርት ዓመትም የቀድሞ ተማሪዎች ሕብረት ይህን በጎ ሥራ ለማስቀጠል ከዚህ በታች ያለውን ዕቅድ አውጥቶ በየዓመቱ የሚያደርገውን የገቢ ማሰባሰቢያ መርሃ ግብር ጀምሯል። እርስዎም ይሳተፉ ለወዳጆችዎም ያጋሩ!!

በዚህ ለ8ተኛ ጊዜ በሚደረገው “የጣና ቤተሰብ ስኮላርሽፕ” ድጋፍ የሚከተሉትን 5 ዕቅዶች ለማከናወን ታስቧል፦

የጣና ሐይቅ የቀድሞ ተማሪዎች ህብረት- የ2017 ዓ.ም ዕቅድ

1. በትምህርት ውጤትና በቤተሰብ ገቢ ሁኔታ የተመረጡ 32 ተማሪዎችን ለአንድ ዓመት በወጪ ማገዝ ከመስከረም – ሰኔ ለእያንዳንዳቸው 1000 ብር (10 ወር * 32 ተማሪዎች * 1000 ብር) – 320,000 ብር

2. ለ 250 እገዛ ለሚያስፈልጋቸው ሴት ተማሪዎች የንጽህና መጠበቂያ (Sanitary Pads) ለአንድ ዓመት ማቅረብ 200,000 ብር

3. ለ5 ዓይነ ስዉራን ተማሪዎች ለትምህርታቸው የሚረዳ የድምፅ መቅጃ መሳሪያ መግዛት 35,000 ብር

4. ወደ ዩኒቨርሲቲ ተመድበው ለሚገቡ እገዛ ለሚያስፈልጋቸው ተማሪዎች ድጋፍ ማድረግ እና የጣና ቤተሰብ ስኮላርሺፕ ተማሪዎች ህክምና መጠባበቂያ በጀት 70,000 ብር

5. የህብረቱን ስራዎች ባህር ዳር ላይ ለሚሰራ ጸሐፊ የዓመት ደሞዝ ከመስከረም እስከ ነሐሴ 3000*12ወር= 36,000 ብር

በድምሩ 661,000 ብር የሚገመት ወጪ በማድረግ እነዚህን ሥራዎች ለማሳካት ታቅዷል፡፡ እስካሁን ባለፉት 7 ዙሮች የነበረው የተማሪዎች እገዛ የተሳካው ይህን በጎ ሥራ የሰሙና የወደዱ ሁሉ ባደረጉት ያላሰለሰ የገንዘብ ፣ የሃሳብ እንዲሁም የጉልበት ድጋፍ ነው፡፡ በመሆኑም 8ተኛውን ዙር በተሻለ ሁኔታ ለማሳካት ጥሪ ስናቀርብ ድጋፋችሁ እንደማይለየን በመተማመን ነው። (ከዚህ በፊት በጣና ቤተሰብ ስኮላርሽፕ የታገዙና ዩንቨርስቲ የገቡ ተማሪዎችን አስተያየት በYouTube ገፃችን ለማየት ይህንን ይጫኑ)

ኢትዮጵያ ውስጥ ያላችሁ በቀጥታ በሚከተሉት የሕብረቱ የጋራ የባንክ አካውንቶች ማስገባት ትችላላችሁ፤

የንግድ ባንክ አካውንት ቁጥር (CBE Account )-  1000408845622

፟የዘሌ ገንዘብ ማስተላለፊያ :- በህብረቱ ኢሜል አድራሻ tanagraduates@gmail.com

Join our telegram group – THAN TELEGRAM

Or use other donation options on our website HERE

https://gofund.me/beee03e9

7ኛው ዙር የጣና ቤተሰብ ስኮላርሺፕ ጥር 2015 ዓ/ም

6ኛው ዙር የጣና ቤተሰብ ስኮላርሺፕ ጥር 2015 ዓ/ም

5ኛው ዙር የጣና ቤተሰብ ስኮላርሺፕ ጥር 2015 ዓ/ም

የ7ኛው ዙር የጣና ቤተሰብ ስኮላርሺፕ አሸናፊ ተማሪዎች እውቅና የመስጠት መርሃግብር ተካሄደ

የዚህ ዓመት የጣና ቤተሰብ ስኮላርሺፕ (Tana Family Scholarship – TFS) የእውቅና መርሃ ግብር ታህሳስ 4 2016 ዓ/ም በጣና ሃይቅ ት/ቤት፣ አሸናፊ ተማሪዎች፣ የትምህርት ቤቱና የህብረቱ አመራሮች በተገኙበት  ተካሂዷል። 

በመርሃግብሩ ላይ ስለመርሃግብሩ አጭር ማብራሪያ  በህብረቱ የባህር ዳር ቢሮ አስተባባሪ አቶ አዱኛ ነጮ የተሰጠ ሲሆን ለእንግዶችና ለተሸላሚ ተማሪዎች የእንኳን ደህና መጣችሁ መልእክት አስተላልፈዋል። 

በመቀጠልም፣ እንግዶችን ያስተዋወቁ ሲሆን በዝግጅቱ ላይ የተገኙት፣ ከህብረቱ መስራችና አመራር  አንዱና በአሜሪካን አገር ነዋሪ የሆኑት ዶ/ር ጌታ መሃሪው እና የትምህርት ቤቱ ርዕሰ መምህር አቶ ሙጨ ባዘዘው ናቸው። 

ዶ/ር ጌታ ለተሸላሚ ተማሪዎች ባስተላለፉት መልዕክት፣ ህብረቱ ድጋፍ የሚያደርገው ተማሪዎችን ለማበረታታትና በድጋፍ ማጣት ምክንያት ጎበዝ ተማሪዎች ከትምህርት ገበታቸው እንዳይቀሩ ለማድረግ እንዲሁም ተማሪዎቹ ትምህርታቸውን ጨርሰው ወደስራ አለም ሲሰማሩ ተመሳሳይ ነገር ለሌሎች ድጋፍ እንዲያደርጉ አርአያ ለመሆን መሆኑን የገለጹ ሲሆን በዚህ አስቸጋሪ ወቅት ተግዳሮቱቹን ተቋቁመው ለዚህ አመት የጣና ቤተሰብ ስኮላርሽፕ ሽልማት አሸናፊ በመሆናቸው አድናቆታቸውን ገልጸውላቸዋል።

በመጨረሻም የምስክር ወረቀት በእንግዶች የተሰጠ ሲሆን የትውውቅና የሻይ ቡና መርሃግብር በማከናወን ዝግጅቱ ተጠናቋል።

ይህ ድጋፍ እንዲሳካ በብዙ የደከማችሁ፣ የህብረቱ አባላትና አመራሮች፣ በጎ አድራጊዎች፣ የት/ቤቱ እመራሮችና የባህር ዳር አስተባባሪዎችን በሙሉ ከልብ እናመሰግናለን::  

ቀና ተሳትፏችሁን በቋሚነት ለመቀጠል በድረገፃችን ላይ የሚገኘውን የአባልነት ፎርም እንድትሞሉም እንጋብዛለን https://tanahaikbdr.com/contacts/

አድራሻዎቻችን፦

የዚህ ዓመት የጣና ቤተሰብ ስኮላርሽፕ አሸናፊ ተማሪዎች የሚከተሉት ናቸው። 

10ኛ ክፍል

  1. ተመስገን አማረ
  2. ሃና አዳነ
  3. ፋሲካ ሙሉ
  4. ነሲቡ በላይነህ
  5. አስፋው በቀለ
  6. ደመቀች ዋሴ
  7. ቤተልሄም ጋሻው
  8. ማሩ አለማንተ

11ኛ ክፍል

  1. ፍቅርተማርያም ታምሩ
  2. መቅደስ በላይነህ
  3. ሮዛ ጓዴ
  4. ፍሬገነት በቀለ
  5. ፍቃዱ ቤዛ
  6. ዳዊት ማሃባው
  7. ኤደን ገ/ሂወት
  8. ይትባረክ መልካሙ

12ኛ ክፍል

  1. አገር አምላክ
  2. መዝገቡ ውበት
  3. በሪሁን ምትኬ
  4. ቅድስት ማሩ
  5. አእምሮ ታደሰ
  6. ስማኮነ መላክ
  7. ስመኘው አጉማስ
  8. ልቦና እንደሻው

1ኛ ዓመት ኮሌጅ የሚገቡ

  1. ሃይለማሪያም ሉሉ
  2. ሙሉቀን ተሻገር
  3. ምንታምር በለጠ
  4. ፈንታሁን ሞላ
  5. መስፍን አስፋው
  6. መርድያ በለጠ
  7. መላከሰላም ላዋየው
  8. ኢዮብ መለሰ

በህብረት ለታናናሾቻችን የተሻለ ነገን እናውርስ!

ሪፖርተር፦ አዱኛ ነጮ ከባህር ዳር