





እህታችን ኮሚሽነር ዮዲት ገዳሙ (Commissioner Yodit Gedamu currently sits on the Governor of Maryland’s Commission on African Affairs) ትውልድ እና እድገቷ አሜሪካን ሀገር ቢሆንም የጣና ሐይቅ የቀድሞ ተማሪዎች ሕብረትን ዓላማ በመደገፍ አብራን ቆይታለች፡፡ሰሞኑን ወደ ኢትዮጵያ በሄደችበት አጋጣሚ ት/ቤቱን ተዘዋውራ ለመጎብኘትና ተማሪዎችና መምህራንን ምሳ ለመጋበዝ አስባ ተነጋግረን ፕሮግራም አመቻችተናል፡፡ በታቀደው መሰረት አርብ ግንቦት 26 2014ዓ/ም ት/ቤቱን በመጎብኘት፤ ግንቦት 27 2014 ዓ/ም ተማሪዎችንና መምህራንን በአዲስ አምባ ሆቴል ምሳ ጋብዛ ጥሩ ውይይት አድርገዋል፡፡ በተማሪዎቹ ስም እናመሰግናለን፡፡
ዝግጅቱ እንዲሳካ የደከሙትን የሕብረቱ የባህርዳር አስተባባሪዎችም ከልብ እናመሰግናለን::
ት/ቤቱን እና ተማሪዎችን ለመደገፍ እንዲሁም የሚሰሩ ሌሎች ስራዎችን ለመደገፍ ከእኛ ጋር እንደምትሰሩ በሙሉ ልባችን እንተማመናለን። ቀና ተሳትፏችሁን በቋሚነት ለመቀጠል በድረገፃችን ላይ የሚገኘውን የአባልነት ፎርም እንድትሞሉም እንጋብዛለን(https://tanahaikbdr.com/contacts/)
የጣና ሐይቅ የቀድሞ ተማሪዎች ሕብረት








