The first Tana Family Scholarship (TFS) was officially launched on September 30 2017. Enjoy the pictures!
የጣና ቤተሰብ ስኮላርሺፕ ገንዘብ የማሰባሰብ ዘመቻ ዛሬ ተጠናቋል።
በዕለተ ቅዳሜ ሰኔ 17፤ 2009 ዓ.ም. ዘጠኝ የጣና ሃይቅ የቀድሞ ተማሪዎች በስካይፒ ተሰባስበው መከሩ። አስተምራ ለዚህ ላበቃችን ት/ቤት እንዴት ውለታዋን እንክፈል በሚል ብዙ ሃሳቦች ተነሱ፤ ብዙ ውይይት ተካሄደ። በሶስት ዋና ዋና መስኮች ት/ቤቱንና ተማሪዎችን ለመደገፍ ውሳኔ ላይ ተደረሰ።
ከነዚህ ውስጥ በቅድሚያ በመጀመሪያ ልንሰራው ያሰብነው ስኮላርሺፕ ማቋቋምና ቢያንስ 24 ተማሪዎችን በየዓመቱ የገንዘብና የማቴሪያል ድጋፍ ማድረግ እንዲሆን ተወስኖ ይህንንም ለማሳካት የገንዘብ ማሰባሰብ ስራ ከሰኔ 21 2009ዓም ጀምሮ ሲሰራ ቆይቷል። ለስኮላርሺፑ ያስፈልጋል ከተባለው 12,000 የአሜሪካ ዶላር ውስጥ 80 የቀድሞ ተማሪዎችና ወዳጆች 9,200 ዶላር በማዋጣት የዕቅዳችንን 77% ማሳከት ተችሏል። በዕውነቱ ይህንን ዕቅድ ለማሳካት በኢትዮጵያና በተለያዩ የውጭ ሃገራት ያላችሁ የቀድሞ ተማሪዎችና የሃሳቡ ደጋፊዎች ያሳያችሁት መነሳሳት እጅግ የሚያስደስትና የሚያኮራ ነው። አዘጋጅ ኮሚቴውም ሰለቸኝ ደከመኝ ሳይል ይህንን ዕቅድ ወደ ተግባር ለመቀየር ሲደክም ቆይቷል።
አዘጋጅ ኮሚቴው በየሁለት ሳምንቱ (አንዳንዴም በየሳምንቱ) የስካይፒ ስብሰባ በመጥራት ማንኛውም የህብረቱ ኣባል እንዲሳተፍ በማድረግ አመርቂ ስራዎችን ሰርቷል። ከነዚህም ውስጥ፤
በዋናነት ይጠቀሳሉ።
ይህ ሁሉ መሆን የቻለው እናንተ ባደረጋችሁት ከፍተኛ ተሳትፎ ነው። በተለይ ባህርዳር ላይ የህብረቱ ተወካይ ላቀ እንዳለው የግል ስራውን ሁሉ በመበደል ይህ እቅድ ከዳር እንዲደርስ የከፈለው መስዋዕትነት እጂግ የሚደንቅ ነው።
ከጐናችን በመቆም ላበረታታችሁን፤ ቃላችንን አምናችሁ ገንዛባችሁንና ጊዜአችሁን ሳትሳሱ ለደገፋችሁን የከበረ አክብሮታችን ይድረሳችሁ። ጣና ሃይቅ ት/ቤት ባትማሩም በሃሳባችን ተስማምታችሁ ድጋፍ ላደረጋችሁልን በሙሉ እጅግ በጣም እናመሰግናለን። ለቀና ተሳትፏችሁ እውቅና መስጠት ስላለብን በህብረቱ ስም የምስጋና ሰርተፊኬት በማዘጋጀት ላይ ነን። በት/ቤቱም ውስጥ ቀጣይነት ባለው መልኩ በየዓመቱ የሚደረገው አስተዋጽዖ እንደማስታወሻ በመዝገብ እንዲቀመጥ ጥረት እያደረግን ነው።
በቀጣይ ሪፖርታችን ላይ የተሸለሙ ተማሪዎችን ስም ዝርዝርና አጠቃላይ የኦዲት ሪፖርት ይዘን እንቀርባለን። ት/ቤቱንና ተማሪዎችን ለመደገፍ የሚሰሩ ሌሎች ስራዎንን ለመደገፍ ከእኛ ጋር እንደምትሰሩ በሙሉ ልባችን እንተማመናለን። ቀና ተሳትፏችሁን በቋሚነት ለመቀጠል በድረ ገፃችን ላይ የሚገኘውን የአባልነት ፎርም እንድትሞሉም እንጋብዛለን (https://tanahaikbdr.com/contacts/ )።
አጠቃላይ የህብረቱ የሒሣብ ሪፖርት (https://tanahaikbdr.com/balance/)
ከዚህ በታች አጠቃላይ የሂሳብ ሪፓርት ቀርቧል (June 28, 2017 to Sept 17, 2017)፤
አጠቃላይ ገቢ
1. በጎ-ፈንድ-ሚ ኣካውንት የተሰበሰበ = $9,200 የአሜርካ ዶላር (Donation list) receipt
አጠቃላይ ድምር= $10,025.33 የአሜርካ ዶላር
አጠቃላይ ወጪ
* በዛሬ ምንዛሬ መሰረት መስከረም 07,2010 ዓ.ም (September 17, 2017 11:30am EST)
በጋራ ዓላማችን እንደምናሳካ እርግጠኞች ነን!
ከአክብሮት ጋር እናመሰግናለን።
የህብረቱ አስተባባሪዎች