ዛሬ ተሸልመዋል

ቅዳሜ ታህሳስ 4,2012 ዓ/ም የ3ተኛው ዙር የጣና ቤተሰብ ስኮላርሺፕ አሸናፊዎችን ሸልመናል፡፡ የሽልማት ሥነ ስርዓቱ ባህርዳር ከተማ በሚገኘው ደሴት ሎጅ ላይ በሚያምር ሁኔታ ተካሂዷል ፡፡ በዚህ ሽልማት ከ10ኛ እስከ 12 ተኛ ክፍል ያሉ አሸናፊ ተማሪዎች የእውቅና ሰርተፍኬት ተሰጥቷቸዋል። ለአሸናፊዎቹ ዓመቱን ሙሉ ለትምህርት ወጪያቸው የሚረዳ የገንዘብ ድጋፍ ማድረግ ተጀምሯል፡፡
ለዚህ ዝግጅት የምሳ እና የቦታ ድጋፍ ያደረገልን የደሴት ሎጅ ባለቤት አቶ ገነቱ ባሳዝነው እና በህትመት ሥራዎች የተባበረን የTana Advertising and Entertainment ባለቤት አቶ ግዛቸው ያየህራድ ከፍ ያለ ምስጋና ይገባቸዋል።በበጎ ፈቃደኝነት ኃላፊነት ወስደው ዝግጅቱን ያሳኩ የቀድሞ ተማሪዎችም ምስጋና ይገባቸዋል፡፡
ትቤቱንና ተማሪዎችን ለመደገፍ የሚሰሩ ሌሎች ስራዎንን ለመደገፍ ከእኛ ጋር እንደምትሰሩ በሙሉ ልባችን እንተማመናለን። ቀና ተሳትፏችሁን በቋሚነት ለመቀጠል በድረገፃችን ላይ የሚገኘውን የአባልነት ፎርም እንድትሞሉም እንጋብዛለን(https://tanahaikbdr.com/contacts/)

https://tanahaikbdr.com/donate/

የመጀመሪያው ዙር የጣና ቤተሰብ ስኮላርሺፕ (2010ዓ.ም) ተሸላሚ የነበሩና በቀድሞ ተማሪዎች ህብረት ሲታገዙ የነበሩ ተማሪዎች ሃሳባቸውን በዚህ ቪዲዮ  ያካፍላሉ።
Please invite more friends to join THAN viber group –
በህብረት ለታናናሾቻችን የተሻለ ነገን እናውርስ!

የጣና ቤተሰብ ስኮላርሺፕ የ2012 ዓ/ም አሸናፊ ተማሪዎች ታወቁ

የ2012 ዓ/ም የጣና ቤተሰብ ስኮላርሺፕ አሸናፊ ተማሪዎች ታወቀዋል።  አሸናፊዎችን ለመለየት ለወንዶች ከ80%፣ ለሴቶች ከ78%፣ እና ለአካል ጉዳተኞች ከ75% በላይ ወጤት ያላቸው ተማሪዎች አንዲያመለክቱ ጥሪ ተደርጎ ነበር። በስኮላርሺፑ መመዘኛ መሰረት የሚከተሉት ተማሪዎች አሸናፊ ሆነው ተመርጠዋል።

10ኛ ክፍል :
  • 1- ሙራድ ኑሩ
    2- ጠብቀው ውበት
    3- ሀይማኖት ምናለ
    4- ቤቴልሄም ጌታቸው
    5- አልማዝ መንጌ
    6- ሰለሞን ነጋ
11ኛ ክፍል:
  • 1- ሕይወት ይልቃል
    2- ሙሉቀን ዘመነ
    3- ደመቀ አስቻለ
    4- ኤልሳቤት ጌታቸው
    5- መታደል ሀይማኖት
    6- ሠርካለም እውነቴ
12ኛ ክፍል:
  • 1- ሙላቱ ዘሪሁን
    2- ገሊላ ብዙአየሁ
    3- ብርሃነመስቀል ወርቁ
    4- አወቀ ጋሻው
    5- ጴጥሮስ ጌታቸው
    6- ማህሌት ሰሙ
ድር ቢያብር ነውና ብሂሉ የሁሉም ሰው ተሳትፎ ለስኬት ያበቃናል:: በዚህ በጎ ሃሳብ ላይ የተሳተፋችሁትን ሁሉ እናመሰግናለን፡፡ በተለይም ደግሞ ከግል ጊዜያቸው ቀንሰው የዚህን መት ሸናፊዎችን 
የመረጡልን ሌሎች ስራዎችን ያገዙን አስተባባሪዎች:-
  • መሰረት አጅጉ 
  • ስለሽ ምናየሁ 
  • መላኩ ባሳዝነው
  • በሃይሉ ይርጋ እና 
  • ያሬድ ምትኩ

እንዲሁም የትምህርት ቤቱን አስተዳደር እናመሰግናለን፡፡

ትቤቱንና ተማሪዎችን ለመደገፍ የሚሰሩ ሌሎች ስራዎንን ለመደገፍ ከእኛ ጋር እንደምትሰሩ በሙሉ ልባችን እንተማመናለን። ቀና ተሳትፏችሁን በቋሚነት ለመቀጠል በድረገፃችን ላይ የሚገኘውን የአባልነት ፎርም እንድትሞሉም እንጋብዛለን(https://tanahaikbdr.com/contacts/)

https://tanahaikbdr.com/donate/

በዚህ ቪዲዮ የመጀመሪያው ዙር የጣና ቤተሰብ ስኮላርሺፕ (2010ዓ.ም) ተሸላሚ የነበሩና በቀድሞ ተማሪዎች ህብረት ሲታገዙ የነበሩ ተማሪዎች ሃሳባቸውን ያካፍላሉ።
Please invite more friends to join THAN viber group –
በህብረት ለታናናሾቻችን የተሻለ ነገን እናውርስ!
የህብረቱ አስተባባሪዎች