በዚህ ዓመት ስለሀገራችን የምንሰማው ነገር በጣም አሳዛኝ ሆኗል፤ የቀድሞ የጣና ሐይቅ ተማሪዎች ህብረትም ሀገራችን ከዚህ ሁሉ ችግር ተላቃ ሁሉም ዜጋ በፈለገበት ቦታ ያለስጋት የሚኖርበት ዘመን እንዲመጣ ከልብ ይመኛል:: ሁላችንም በያለንበት የማህበረሰባችን ችግር መፍትሄ አካል ለመሆን የተቻለንን እናድርግ::
ከጥቂት ወራት በፊት እደተገለጸው የ2013 ዓ.ም. ዕቅዶችን ለማሳካት ከአባላት ገንዘብ ተሰብስቧል፡፡ይህም የዚህን ዓመት አቅማችንን ለማሳደግ ስላገዘን በዚህ ዓመት የሚከተሉተን ማሻሻያዎች ለማድረግ አስተባባሪዎች ወስነዋል::
የ2013 ዓ.ም የጣና ቤተሰብ ስኮላርሽፕ አሸናፊ ተማሪዎችን ብዛት ከ24 ወደ 32 ያሳደግን ሲሆን (ወቅታዊውን ወረርሽኝ በማስመልከት የዚህ ዓመት ማጣሪያ ሂደት በልዩ ሁኔታ ታይቶ ነባር ተማሪዎችን ይዘን ጥቂት አዳዲስ ተማሪዎችን ጨምረናል)፤ ለሴት ተማሪዎች የሚቀርበው የንጽህና መጠበቂያ (Sanitary Pads) ተጠቃሚዎች ቁጥርም ከ150 ወደ 233 ከፍ እንዲል ተደርጓል። ለዚህ እድገት ሁላችሁም አስተዋጽኦ አድርጋችኋልና ከልብ እናመሰግናለን!!
ቀደም ብሎ እንደተገለፀውም ህብረቱ በ18ሺህ ብር ወጪ 5ሺ ሊትር የሚይዝ የውሃ ማጠራቀሚያ (water tank) ለትምህርት ቤቱ አስረክቧል፡፡ እንዲሁም ከዚህ በፊት እንደተደረገው ለተጨማሪ 10 ዓይነስውራን ተማሪዎች የድምፅ መቅጃ መሳሪያ ለመስጠት በዝግጅት ላይ ነው፡፡
በዚህ መሰረት ለዚህ ዓመት የጣና ቤተሰብ ስኮላርሺፕ የሚከተሉት ተማሪዎች አሸናፊ ሆነው ተመርጠዋል።
10ኛ ክፍል:
1- ሜሮን ክንዴ
2- ፍቅር ይልቃል
3- ሙሉቀን ተሻገር
4- ፍቅርተ ጌታቸው
5- ኃይለማርያም ልዑል
6- ሀብታሙ ውብሸት
7- ቢኒያም አላምረው
8- ፋሲካው ቢያዝን
11ኛ ክፍል :
1- ቤቴልሃም ደባሱ
2- ቤቴልሄም ጌታቸው
3- አልማዝ መንጌ
4- ሙራድ ኑሩ
5- ጠብቀው ውበት
6- ሀይማኖት ምናለ
7- ሰለሞን ነጋ
8- አማኑኤል ፍስሀ
12ኛ ክፍል:
1- ሕይወት ይልቃል
2- ኤልሳቤት ጌታቸው
3- ሠርካለም እውነቴ
4- እህተሙሴ ነብዩ
5- ሙሉቀን ዘመነ
6- ደመቀ አስቻለ
7- መታደል ሀይማኖት
8- ብሩክ አሰፋ
1ኛ ዓመት ኮሌጅ የሚገቡ:
1- ሊዲያ ነብዩ
2- ማህሌት ሰሙ
3- ገሊላ ብዙአየሁ
4- ብርሃነመስቀል ወርቁ
5- አወቀ ጋሻው
6- ጴጥሮስ ጌታቸው
7- ሙላቱ ዘሪሁን
8- መልካሙ ሙሉአለም
በዚህ በጎ ሃሳብ ላይ በማስተባበር የተሳተፋችሁትን ሁሉ እናመሰግናለን፡፡ በተለይም የባህርዳር አስተባባሪዎችን:-
- መሰረት አጅጉ
- ስለሺ ምንአየሁ
- መላኩ ባሳዝነው
- በሀይሉ ይርጋ እና
- ያሬድ ምትኩ
እንዲሁም የትምህርት ቤቱን አስተዳደር እናመሰግናለን፡፡
ት/ቤቱንና ተማሪዎችን ለመደገፍ የሚሰሩ ሌሎች ስራዎችን ለመደገፍ ሁላችንም አብረን መስራት እንደምንቀጥል በሙሉ ልባችን እንተማመናለን። ቀና ተሳትፏችሁን በቋሚነት ለመቀጠል በድረገፃችን ላይ የሚገኘውን የአባልነት ፎርም እንድትሞሉም እንጋብዛለን (https://tanahaikbdr.com/contacts/)
በዚህ ቪዲዮ የመጀመሪያው ዙር የጣና ቤተሰብ ስኮላርሺፕ (2010ዓ.ም) ተሸላሚ የነበሩና በቀድሞ ተማሪዎች ህብረት ሲታገዙ የነበሩ ተማሪዎች ሃሳባቸውን ያካፍላሉ።
https://youtu.be/Z1eRtSnF0cU
ለበለጠ መረጃ በማህበራዊ ሚዲያ ገፆቻችንን ይከተሉን።
Social media page – THAN facebook page / THAN twitter
Youtube channel – THAN Youtube channel
በህብረት ለታናናሾቻችን የተሻለ ነገን እናውርስ!
የህብረቱ አስተባባሪዎች
