ስድስተኛው የጣና ቤተሰብ ስኮላርሺፕ የሽልማት መርሃ ግብር በተሳካ ሁኔታ ተከናውኗል

የጣና ሐይቅ የቀድሞ ተማሪዎች ህብረት ያዘጋጀው ስድስተኛው የጣና ቤተሰብ ስኮላርሺፕ የሽልማት መርሃ ግብር ጥር 6/2015 ዓ/ም በጣና ሐይቅ ትምህርት ቤት አዳራሽ በተሳካ ሁኔታ ተከናውኗል።

ጊዜያችሁንና ገንዘባችሁን ለሰጣችሁ የህብረቱ አባላት በተማሪዎች ስም እናመሰግናለን። በአካል ተገኝታችሁ ለታዳጊ ወንድም እህቶቻችሁ ምክር የሰጣችሁ፣ልምድ ያካፈላችሁ የቀድሞ ተማሪዎችን በልዩ ሁኔታ እናመሰግናለን፡፡ ዝግጅቱ እንዲሳካ ቀና ትብብር ላደረገው የት/ቤቱን አስተዳደርም ምስጋናችን ከፍ ያለ ነው።

በመርሃ ግብሩ ላይ ለትምህርት ቤቱ የተለያዩ ድጋፍ ያደረጉ የቀድሞ ተማሪዎች ፡ የባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ ሰራተኞች እና መምህራን የምስክር ወረቀት በት/ቤቱን አስተዳደር ተሰጥቷል፡፡

በህብረት ለታናናሾቻችን የተሻለ ነገን እናውርስ!

የጣና ሐይቅ የቀድሞ ተማሪዎች ሕብረት

የጣና ሐይቅ ት/ቤት የቀድሞ ተማሪዎችና ደጋፊዎች በሙሉ ተጋብዛችኋል!

የጣና ሐይቅ የቀድሞ ተማሪዎች ህብረት በኢትዮጵያና በውጭ ሀገር በሚኖሩ በጎ ፈቃደኛ የቀድሞ ተማሪዎች በ2004 ዓ/ም ተጀመረ፡፡ በአሁኑ ጊዜ ህብረቱ ሰፍቶ በተለያዩ ዓመታት በትምህርት ቤቱ የተማሩ፣በተለያዩ የዓለማችን ክፍሎች የሚኖሩ የቀድሞ ተማሪዎችን አቅፎ የተለያዩ እገዛዎችን በመስጠት ላይ ይገኛል፡፡ 

ህብረቱ በየዓመቱ ከሚያከናቸው ተግባራት አንዱ የጣና ቤተሰብ ስኮላርሺፕ ይገኝበታል። በዚህ ዓመትም በላቀ ውጤታቸውና በቤተሰብ ገቢ ሁኔታ የተመረጡ ታዳጊ ተማሪዎች ሽልማት ይሰጣል:: 

እርስዎም ይህን የስድስተኛው ዙር የጣና ቤተሰብ ስኮላርሺፕ አሸናፊዎች ሽልማት በምንሰጥበት ቀን ቅዳሜ ጥር 6/2015 ዓ/ም በጣና ሐይቅ ትምህርት ቤት አዳራሽ ከረፋዱ 4፡00 ሰዓት እንዲገኙልን በአክብሮት ጠርተነዎታል።

በህብረት ለታናናሾቻችን የተሻለ ነገን እናውርስ! 

Social media page – THAN facebook page / THAN twitter 

Youtube channel – THAN Youtube channel

Join us on Telegram

የህብረቱ አስተባባሪዎች