ለ9ኛው ዙር የጣና ቤተሰብ ስኮላርሺፕ (Tana Family Scholarship – TFS) የእውቅና መርኃ ግብር ሀሙስ ጥር 7 2018 ዓ/ም በጣና ሐይቅ ት/ቤት፣ አሸናፊ ተማሪዎች፣ የትምህርት ቤቱና የህብረቱ አመራሮች በተገኙበት ተከናውኗል።
በትምህርት ውጤትና በቤተሰብ ገቢ ሁኔታ የተመረጡ 37 የጣና ቤተሰብ ስኮላርሺፕ አሸናፊ ተማሪዎች ተለይተው የስኮላርሺፕ ሰርተፊኬት ተሰጥቷቸዋል። ተማሪዎቹ የ2018ዓም የትምህርት ዓመት እስከሚያልቅ ወርሀዊ የገንዘብ ድጋፍ ይደረግላቸዋል፡፡
በተጨማሪም 5 ዓይነ ስውራን ተማሪዎች ትምህርታቸውን ለመከታተል የሚያግዙ በእጅ የሚያዙ የመቅረጸ ድምጽ መሳሪያዎች (Voice Recorders) ተረክበዋል።
ሕብረቱ በዓመቱ መግቢያ ላይ ወደ ዩንቨርሲቲ ለሚገቡና እገዛ ለሚያስፈልጋቸው 31 ተማሪዎች ለእያንዳንዳቸው የ3500ብር ድጋፍ አድርጎ ነበር፡፡
በዕለቱ ከህብረቱ መስራቾች በፊንላንድ ሀገር ነዋሪ የሆኑት ዶ/ር ተናገር በቃሉ እና አቶ ምስጋናው ብርሀን፣ እንዲሁም አቶ ቴዎድሮስ ተሠራ ከአሜሪካ፣ ወ/ሮ ማስተዋል አለሙ፣አቶ ተናኘ ፍቅሬ፣አቶ አዱኛ ነጮ ከሀገር ውስጥ በዝግጅቱ ላይ ተገኝተው ለተሸላሚ ተማሪዎች የማበረታቻ መልዕክት አስተላልፈዋል ።
የሕብረቱ አስተባባሪዎች በተማሪዎች እየተሰሩ ያሉ የአይቲ ፕሮጀክቶችን ጎብኝተው ተጨማሪ እገዛ እንደሚያደርጉ ቃል ገብተዋል።
ይህ ድጋፍ እንዲሳካ በብዙ የደከማችሁ፣ የሕብረቱ አባላትና አመራሮች፣ በጎ አድራጊዎች፣ የት/ቤቱን አስተዳደርና የባህር ዳር አስተባባሪዎችን በሙሉ ከልብ እናመሰግናለን::
የአማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን አስኳላ በተባለው ፕሮግራም ለዝግጅቱ የሰጠውን የሚዲያ ሽፋን ከታች ይመልከቱ፡፡
የጣና ሐይቅ የቀድሞ ተማሪዎች ሕብረት






