የ8ኛው ዙር የጣና ቤተሰብ ስኮላርሺፕ አሸናፊ ተማሪዎች እውቅና የመስጠት መርሃግብር ተካሄደ

የ8ተኛው ዙር የጣና ቤተሰብ ስኮላርሺፕ (Tana Family Scholarship – TFS) የእውቅና መርሃ ግብር ጥር 1  2017 ዓ/ም በጣና ሃይቅ ት/ቤት፣ አሸናፊ ተማሪዎች፣ የትምህርት ቤቱና የህብረቱ አመራሮች በተገኙበት  ተካሂዷል። 

በትምህርት ውጤትና በቤተሰብ ገቢ ሁኔታ የተመረጡ 32 የጣና ቤተሰብ ስኮላርሺፕ አሸናፊ ተማሪዎች ተለይተው ሽልማት ተሰጥቷል ፣ በእለቱ ከህብረቱ መስራችና አመራር  አንዱና በአሜሪካን አገር ነዋሪ የሆኑት ዶ/ር ጌታ መሃሪው የተገኙ ሲሆን ለተሸላሚ ተማሪዎች  የማበረታቻ መልዕክት አስተላልፈዋል ።

ይህ ድጋፍ እንዲሳካ በብዙ የደከማችሁ፣ የህብረቱ አባላትና አመራሮች፣ በጎ አድራጊዎች፣ የት/ቤቱ እመራሮችና የባህር ዳር አስተባባሪዎችን በሙሉ ከልብ እናመሰግናለን::  

ቀና ተሳትፏችሁን በቋሚነት ለመቀጠል በድረገፃችን ላይ የሚገኘውን የአባልነት ፎርም እንድትሞሉም እንጋብዛለን https://tanahaikbdr.com/contacts/

አድራሻዎቻችን፦

comment