የጣና ሐይቅ የቀድሞ ተማሪዎች ህብረት ያዘጋጀው ስድስተኛው የጣና ቤተሰብ ስኮላርሺፕ የሽልማት መርሃ ግብር ጥር 6/2015 ዓ/ም በጣና ሐይቅ ትምህርት ቤት አዳራሽ በተሳካ ሁኔታ ተከናውኗል።
ጊዜያችሁንና ገንዘባችሁን ለሰጣችሁ የህብረቱ አባላት በተማሪዎች ስም እናመሰግናለን። በአካል ተገኝታችሁ ለታዳጊ ወንድም እህቶቻችሁ ምክር የሰጣችሁ፣ልምድ ያካፈላችሁ የቀድሞ ተማሪዎችን በልዩ ሁኔታ እናመሰግናለን፡፡ ዝግጅቱ እንዲሳካ ቀና ትብብር ላደረገው የት/ቤቱን አስተዳደርም ምስጋናችን ከፍ ያለ ነው።
በመርሃ ግብሩ ላይ ለትምህርት ቤቱ የተለያዩ ድጋፍ ያደረጉ የቀድሞ ተማሪዎች ፡ የባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ ሰራተኞች እና መምህራን የምስክር ወረቀት በት/ቤቱን አስተዳደር ተሰጥቷል፡፡
በህብረት ለታናናሾቻችን የተሻለ ነገን እናውርስ!
የጣና ሐይቅ የቀድሞ ተማሪዎች ሕብረት































































