የጣና ሐይቅ የቀድሞ ተማሪዎች ህብረት የ2014 ዓ.ም ዕቅድ መሰረት የሚከተሉትን ስራዎች አጠናቁዋል :-
- የ5ተኛው ዙር የጣና ቤተሰብ ስኮላርሽፕ 32 አሸናፊ ተማሪዎችን በመለየት ሸልሟል፣
- ለ261 ሴት ተማሪዎች ንጽህና መጠበቂያ (Sanitary Pads) የመግዛት አቅም ለሌላቸው እገዛ አድርጓል፣
- ለ5 ዓይነ ስዉራን ተማሪዎች ለትምህርታቸው የሚረዳ የድምፅ መቅጃ መሳሪያ አቅርቧል፣
- ከ105 ሺህ ብር በላይ ወጪ በማድረግ 5,000 ሊትር የሚይዝ የውሃ ማጠራቀሚያ (water tank) በመግዛት እንዲሁም የትምህርት ቤቱን የቧንቧ መስመር አሰርቶ ለአገልግሎት አብቅቷል::
ለሥራው መሳካት የተባበሩትን በሙሉ ከልብ እናመሰግናለን::
ት/ቤቱን እና ተማሪዎችን ለመደገፍ እንዲሁም የሚሰሩ ሌሎች ስራዎችን ለመደገፍ ከእኛ ጋር እንደምትሰሩ በሙሉ ልባችን እንተማመናለን። ቀና ተሳትፏችሁን በቋሚነት ለመቀጠል በድረገፃችን ላይ የሚገኘውን የአባልነት ፎርም እንድትሞሉም እንጋብዛለን(https://tanahaikbdr.com/contacts/)
YouTube/Facebook: Tana Haik Alumni Network
Twitter: @HaikTana
በህብረት ለታናናሾቻችን የተሻለ ነገን እናውርስ!
የጣና ሐይቅ የቀድሞ ተማሪዎች ሕብረት
ታህሳስ 2014 ዓ.ም