የጣና ሐይቅ የቀድሞ ተማሪዎች ህብረት- የ2014 ዓ.ም ዕቅድ

የጣናሐይቅ የቀድሞ ተማሪዎች ህብረት በየዓመቱ የሚያደርገውን  የገንዘብ ማሰባሰቢያ መርሃ ግብር ለመጀመር ዝግጅቱን ጨርሷል። በእዚህ ለ5ተኛ ጊዜ በሚደረገው “የጣና ቤተሰብ ስኮላርሽፕ” ድጋፍ የሚከተሉትን ዕቅዶች ለማከናወን ታስቧል፦

1- የ5ተኛው ዙር የጣና ቤተሰብ ስኮላርሽፕ አሸናፊ  32 ተማሪዎችን መሸለም:-ከመስከረም – ሰኔ       
    ለያንዳንዳቸው 700 ብር  (10 ወር * 32 ተማሪዎች * 700 ብር)  – 224,000 ብር  (~$ 5,209)
2- ለ 250 የገንዘብ እጥረት ላለባቸው ሴት ተማሪዎች የንጽህና መጠባቂያ (Sanitary Pads) ለአንድ 
    ዓመት ማቅረብ – 85,000 ብር (~$1,977)
3- ለ4 ዓይነ ስዉራን ተማሪዎች ለትምህርታቸው የሚረዳ የድምፅ መቅጃ መሳሪያ መግዛት: 8,000
  ብር (~$186)
4- ወደ ዩኒቨርሲቲ ተመድበው ለሚገቡ እገዛ ለሚያስፈልጋቸው ተማሪዎች ድጋፍ ማድረግ እና የጣና ቤተሰብ ስኮላርሺፕ ተማሪዎች ህክምና መጠባበቂያ በጀት – 35,000 ብር  (~$814) 
5- የህብረቱን ስራዎች ባህር ዳር ላይ ለሚሰራልን ተማሪ የዓመት ደሞዝ ከመስከረም እስከ ነሐሴ –   
      1,200 ብር *12 ወር= 14,400 ብር (~$335)

በድምሩ 366,400ብር ወይም $8,521 ዶላር የሚገመት ወጪ በማድረግ እነዚህን ሥራዎች ለማሳካት ታቅዷል፡፡ እስካሁን ባለፉት 4 ዙሮች የነበረው የተማሪዎች እገዛ የተሳካው ይህን በጎ ሥራ የሰሙና የወደዱ ሁሉ ባደረጉት ያላሰለሰ የገንዘብ ፣ የሃሳብ እንዲሁም የጉልበት ድጋፍ ነው፡፡ በመሆኑም  5ተኛውን ዙር በተሻለ ሁኔታ ለማሳካት ጥሪ ስናቀርብ ድጋፋችሁ እንደማይለየን በመተማመን ነው።

Note : *Bank exchange rate used for estimate 1$ = 43 Birr

ኢትዮጵያ ውስጥ ያላችሁ ቀጥታ በሚከተሉት ህብረቱ የጋራ የባንክ አካውንቶች ማስገባት ትችላላችሁ፤
– የንግድ ባንክ አካውንት ቁጥር፤ 1000408845622
 – የዳሽን ባንክ አካውንት ቁጥር፤ 5020904670002 

Or use other options here: https://tanahaikbdr.com/donate/

Tana Family Scholarship – 5th Round Gofundme – CLICK HERE

Social media page – THAN facebook page THAN Twitter page
Youtube channel – THAN Youtube channel 
To be a member please fill membership form – HERE 
CLICK HERE TO JOIN US ON VIBER

ከአክብሮት ጋር!

የህብረቱ አስተባባሪዎች! https://tanahaikbdr.com/about/