የ4ተኛው ዙር ሽልማት ተካሄደ

የ4ተኛው ዙር የጣና ቤተሰብ ስኮላርሺፕ አሸናፊ ተማሪዎች የሽልማት ሥነስርዓት ተካሄደ፡፡ ሥነስርዓቱ እሮብ ጥር 5 ቀን የቀድሞ ተማሪዎች ህብረት አስተባባሪዎች፣ መምህራንና ተሸላሚ ተማሪዎች በተገኙበት በጣና ሐይቅ ት.ቤት አዳራሽ ተካሂዷል፡፡ ለ32 ተማሪዎች የሽልማት ሰርተፊኬት የተሰጠ ሲሆን ሙሉ የትምህርት ዓመቱን ለትምህርት ወጪያቸው በየወሩ የገንዘብ ድጋፍ ይደረግላቸዋል፡፡ በተጨማሪም ህብረቱ በዚህ ዓመት ለ233 ሴት ተማሪዎች የሞዴስ አቅርቦት ማድረግ ጀምሯል፡፡ እንዲሁም እንደከዚህ በፊቱ ለተጨማሪ 10 ዓይነስውራን ተማሪዎች የድምፅ መቅጃ መሳሪያ ገዝቶ አቅርቧል፡፡

ተሸላሚ ተማሪዎችና የቀድሞ ተማሪዎች (ተጨማሪ ፎቶዎችን ከታች ይመልከቱ)

ለሥራው መሳካት የተባበሩትን የት.ቤቱን አስተዳደር፥ጣና የህትመትና ማስታወቂያ ድርጅትን፣ ጎዶሊያስ ሬስቱራንትንና ግሪን ፋርማሲን ከልብ እናመሰግናለን፡፡ እንዲሁም ዝግጅቱን የግል ጊዜያቸውን ሰውተው በአካል በመገኘት ያሳኩትን የቀድሞ ተማሪዎች ህብረት አስተባባሪዎች፡-

– ስለሺ ምንአየሁ፣ቴዎድሮስ ተሠራ፣ መሰረት እጅጉ፣ ራሄል ወንዴ፣ በሀይሉ ይርጋ፣ ምስጋናው ብርሃን፣ ሳሙኤል አልማው፣ ጌታ መሀሪ፣ ዮናታን ጎሳዬ፣ ሄኖክ ኃይለማርያም እና ያሬድ ምትኩን እናመሰግናለን፡፡ ለታናናሾቻችን ስኬት አብረን እንሥራ!!

የ2013 ዓ ም አራተኛው ዙር የጣና ቤተሰብ ስኮላርሺፕ አሸናፊ ተማሪዎች

comment