የጣና ሐይቅ የቀድሞ ተማሪዎች ህብረት- የ2013 ዓ.ም እቅድ

የቀድሞ የጣና ሐይቅ ተማሪዎች ህብረት በየዓመቱ በዚህ ወቅት የምናደርገውን የጎፈንድሚ ገንዘብ ማሰባሰቢያ መርሃ ግብር በወቅታዊው ሁኔታ ምክንያት በተለመደው መልኩ ላለማካሄድ ወስነናል፡፡በዚያ ፋንታ አስተባባሪዎች፣አባላትና የማህበሩ ወዳጆች በቀጥታ ወደማህበሩ አካውንት መዋጮ የሚያስገቡበትን አማራጮች አዘጋጅተናል፡፡ የቀጣዩን ዓመት ወጪ ከዚህ መዋጮ እና ከባለፈው ዓመት መጠባበቂያ በጀት በመጠቀም ለመሸፈን አስበናል፡፡ ህብረቱ የሚከተሉትን የ2013 ዓ/ም  ሥራዎች ለማከናወን አቅዷል፦
  1. የ4ተኛው ዙር የጣና ቤተሰብ ስኮላርሽፕ አሸናፊ  24 ተማሪዎችን መሸለም:-ከመስከረም – ሰኔ ለያንዳንዳቸው 500 ብር  (10 ወር * 24 ተማሪዎች * 500 ብር)  – 120,000 ብር (~$3,410)(በዚህ አጋጣሚ በዘጠነኛ ክፍል 6 ተማሪዎች ፋንታ ከጣና ሐይቅ ወደ ኮሌጅ የሚያልፉ 6 የአንደኛ ዓመት ተማሪዎችን ለማገዝ ተወያይተናል፡፡ ስለዚህ 24ቱ ተማሪዎች ከ10ኛ፣11ኛ፣12ኛና ከአንደኛ ዓመት ኮሌጅ የሚመረጡ ይሆናሉ)
  2. ለ 150 የገንዘብ እጥረት ላለባቸው ሴት ተማሪዎች የንጽህና መጠባቂያ (Sanitary Pads) ለአንድ አመት ማቅረብ – 30,000 ብር (~$850)
  3. ለ10 ዓይነ ስዉራን ተማሪዎች ለትምህርታቸው የሚረዳ የድምፅ መቅጃ መሳሪያ መግዛት  – 21,150 ብር (~$600)
  4. ለአካል ጉዳተኛ የጣና ቤተሰብ ስኮላርሽፕ ተሸላሚዎች የክረምት ሁለት ወራት ተጨማሪ እርዳታ ማድረግ እና የ24ቱ ተማሪዎች ህክምና መጠባበቂያ በጀት – 5,300 ብር (~$150)
  5. የህብረቱን ስራዎች ባህር ዳር ላይ ለሚሰራልን ተማሪ የዓመት ደሞዝ ከመስከረም እስከ ነሐሴ – 1,000*12ወር= 12,000 ብር (~350)

በአጠቃላይ የ2013 ዓ.ም የበጀት እቅዳችን 188,450 ብር (~$5,350 USD) ይሆናል፡፡

በተጨማሪም ከዚህ ዓመት ዕቅዶች መካከል ሊሰሩ ታስበው ባለው ወቅታዊ ሁኔታ ምክንያት ለሌላ ጊዜ እንዲተላለፉ የተደረጉ ሁለት ሥራዎች አሉ፦

  • ለትምህርት ቤቱ የመጠጥ ውሃ ማጠራቀሚያ ማስገባት (Water Tank) እና
  • በት/ቤቱ የሚገኘውን የህብረቱን ቢሮ ማስጠገንና መጠቀም ናቸው፡፡ የህብረቱ ዋና ዓላማ ተማሪዎች ላይ መስራት ስለሆነ እነዚህን ከዋናው የዓመት በጀት ውስጥ ሳናካትት በተጠባባቂነት እንይዛቸዋለን፡፡ 

በየአመቱ ለመክፈል ቃል የገባችሁ አባሎች እንዲሁም በዚህ አመት ለመሳተፍ ለምትፈልጉ የማህበሩን  Zelle Account (202 413-4946) ወይም በድረ ገፃችን የቀረቡ አማራጮችን መጠቀም ትችላላችሁ (https://tanahaikbdr.com/donate/

ተማሪዎቹንና ትቤቱን ለመደገፍ ሁላችንም አብረን እንደምንቆም በሙሉ ልባችን እንተማመናለን። ቀና ተሳትፏችሁን በቋሚነት ለመቀጠል በድረገፃችን ላይ የሚገኘውን የአባልነት ፎርም እንድትሞሉም እንጋብዛለን፡፡(https://tanahaikbdr.com/contacts/)

ከአክብሮት ጋር!

የህብረቱ አስተባባሪዎች! https://tanahaikbdr.com/about/

THAN-PLAN-2013

ለበለጠ መረጃ በማህበራዊ ሚዲያ ገፆቻችንን ይከተሉን።

Social media page – THAN facebook page / THAN twitter 

Youtube channel – THAN Youtube channel

CLICK HERE TO JOIN US ON VIBER

comment