ዛሬ ተሸልመዋል

ቅዳሜ ታህሳስ 4,2012 ዓ/ም የ3ተኛው ዙር የጣና ቤተሰብ ስኮላርሺፕ አሸናፊዎችን ሸልመናል፡፡ የሽልማት ሥነ ስርዓቱ ባህርዳር ከተማ በሚገኘው ደሴት ሎጅ ላይ በሚያምር ሁኔታ ተካሂዷል ፡፡ በዚህ ሽልማት ከ10ኛ እስከ 12 ተኛ ክፍል ያሉ አሸናፊ ተማሪዎች የእውቅና ሰርተፍኬት ተሰጥቷቸዋል። ለአሸናፊዎቹ ዓመቱን ሙሉ ለትምህርት ወጪያቸው የሚረዳ የገንዘብ ድጋፍ ማድረግ ተጀምሯል፡፡
ለዚህ ዝግጅት የምሳ እና የቦታ ድጋፍ ያደረገልን የደሴት ሎጅ ባለቤት አቶ ገነቱ ባሳዝነው እና በህትመት ሥራዎች የተባበረን የTana Advertising and Entertainment ባለቤት አቶ ግዛቸው ያየህራድ ከፍ ያለ ምስጋና ይገባቸዋል።በበጎ ፈቃደኝነት ኃላፊነት ወስደው ዝግጅቱን ያሳኩ የቀድሞ ተማሪዎችም ምስጋና ይገባቸዋል፡፡
ትቤቱንና ተማሪዎችን ለመደገፍ የሚሰሩ ሌሎች ስራዎንን ለመደገፍ ከእኛ ጋር እንደምትሰሩ በሙሉ ልባችን እንተማመናለን። ቀና ተሳትፏችሁን በቋሚነት ለመቀጠል በድረገፃችን ላይ የሚገኘውን የአባልነት ፎርም እንድትሞሉም እንጋብዛለን(https://tanahaikbdr.com/contacts/)

https://tanahaikbdr.com/donate/

የመጀመሪያው ዙር የጣና ቤተሰብ ስኮላርሺፕ (2010ዓ.ም) ተሸላሚ የነበሩና በቀድሞ ተማሪዎች ህብረት ሲታገዙ የነበሩ ተማሪዎች ሃሳባቸውን በዚህ ቪዲዮ  ያካፍላሉ።
Please invite more friends to join THAN viber group –
በህብረት ለታናናሾቻችን የተሻለ ነገን እናውርስ!

comment