የ2011 የጣና ቤተሰብ ስኮላርሺፕ ይመክፈቻ መርሃ ግብር

ጤና ይስጥልን ውድ የጣና ሐይቅ ት/ቤት ወዳጆች!

ለ2011 የጣና ቤተሰብ ስኮላርሺፕ መሳካት ድጋፍ ላደረጋችሁልን በሙሉ፣ ስላደረጋችሁት ነገር ሁሉ በፈጣሪ ስም አክብሮታችን ይድረሳችሁ። የዚህ አመት ገንዘብ የማሰባሰብ ዘመቻ ጥቅምት 30 2011 (November 09 2018) የተጠናቀቀ ሲሆን፡  በተመቻቹህ ጊዜ ድጋፍ መስጠት ለምትፈልጉ በግል ልትፅፉልን እንደምትችሉ ልናሳስባችሁ እንወዳለን።

በዚሁ አጋጣሚ የፊታችን እሁድ የአመቱ ስኮላርሺፕ አሸናፊዎችን እውቅና የምንሰጥበት አጠር ያለ የምሳ መርሃ ግብር በፓልም ፓላስ ሆቴል እንዳዘጋጀን ልንገልፅላችሁ እንወዳለን። በመርሃ ግብሩ ላይም ሳይሰለቹ ድጋፍ እየሰጡን የሚገኙ ጥቂት የቀድሞ እና የአሁን መምህራን ይገኛሉ።  የመርሃ ግብሩን አጠቃላይ ውሎ የሚያሳዩ ፎቶዎች ወይም ቪዲዮዎች እንደደረሱን ድረ ገፆቻችን ላይ በመለጠፍ እንድትመለከቱት እናደርጋለን። ይህንን የምሳ ወጭ ሙሉ በሙሉ የሚሸፍንልን የፓልም ፓላስ ሆቴል ባለቤት አቶ አለምሰገድ ድጋፌ ነው። አቶ አለምሰገድ ድጋፌ የተማረበትን ት/ቤት አስቦ አለኝታነቱን ስላሳየን በጣና ሀይቅ የቀድሞ ተማሪዎች ህብረት ስም ልባዊ ምስጋናችንን እናቀርባለን።

ከአክብሮት ጋር!
የህብረቱ አስተባባሪዎች!
ለበለጠ መረጃ በማህበራዊ ሚዲያ ገፆቻችንን ይከተሉን።

ፌስቡክ ትዊተር