Call for Tana Family Scholarship Application

ለጣና ሐይቅ ት.ቤት ተማሪዎች
ሁለተኛው ዙር የጣና ቤተሰብ ስኮላርሽፕ ምዝገባ ተጀመረ !

ከሀገር ውጪና በሀገር ውስጥ የምንኖር የቀድሞ የጣና ሐይቅ ተማሪዎች “የጣና ሐይቅ የቀድሞ ተማሪዎች ህብረትን” (Tana Haik Alumni Network) አቋቁመን ለጣና ሐይቅ ት/ቤትና ተማሪዎች የተለያዩ ድጋፎች ለማድረግ እየተንቀሳቀስን እንገኛለን፡፡ ከነዚህ ድጋፎች ውስጥ በሚጠናቀቀው ዓመት 2010ዓ.ም የተጀመረው የጣና ቤተሰብ ስኮላርሽፕ (Tana Family Scholarship) ይገኝበታል፡፡ ለመጪው የ2011ዓም የሁለተኛ ዙር ስኮላርሽፕ ተሸላሚዎችን ለመለየት ዝግጅት ጀምረናል፡፡ በዚህም መሰረት በቀጣዩ ዓመት ከ10ኛ-12ኛ ክፍል የሚማሩ ተማሪዎችን ለመቀበል ተዘጋጅተናል፡፡ለዚህ የስኮላርሺፕ ሽልማት ማመልከት የምትፈልጉ ተማሪዎችን ህብረቱ በሚከተለው መስፈርት መሰረት መዝግቦ ለመቀበልና ለመለየት ወስኗል፡፡

መስፈርት

  • ወንድ ተማሪዎች፦ በ2010 ዓ.ም በጣና ሐይቅ ት.ቤት የመጀመሪያ ሴሚስተር አማካይ ውጤት 80% እና ከዚያ በላይ ያመጣችሁ
  • ሴት ተማሪዎች፦ በ2010ዓ.ም በጣና ሐይቅ ት.ቤት የመጀመሪያ ሴሚስተር አማካይ ውጤት 78% እና ከዚያ በላይ ያመጣችሁ
  • አካል ጉዳተኛ ተማሪዎች፦ በ2010ዓ.ም በጣና ሐይቅ ት.ቤት የመጀመሪያ ሴሚስተር አማካይ ውጤት 75% እና ከዚያ በላይ ያመጣችሁ

ከላይ የተጠቀሰውን መስፈርት የምታሟሉ የ2011 10ኛ፣11ኛ እና 12ተኛ ክፍል ተማሪዎች የተማሪ መታወቂያና የውጤት ካርድ ኮፒ በመያዝ ከሰኔ 25 እስከ ሐምሌ 10, 2010 ዓ.ም በት.ቤቱ ግቢ በሚገኘው የቀድሞ ተማሪዎች ህብረት ቢሮ ቀርባችሁ ፎርም መሙላትና መመዝገብ እንደምትችሉ እንገልፃለን፡፡

የጣና ሐይቅ የቀድሞ ተማሪዎች ኅብረት
Tana Haik Alumni Network (THAN)

comment