የጣና ቤተሰብ ስኮላርሺፕ ገንዘብ የማሰባሰብ ዘመቻ ዛሬ ተጠናቋል።
በዕለተ ቅዳሜ ሰኔ 17፤ 2009 ዓ.ም. ዘጠኝ የጣና ሃይቅ የቀድሞ ተማሪዎች በስካይፒ ተሰባስበው መከሩ። አስተምራ ለዚህ ላበቃችን ት/ቤት እንዴት ውለታዋን እንክፈል በሚል ብዙ ሃሳቦች ተነሱ፤ ብዙ ውይይት ተካሄደ። በሶስት ዋና ዋና መስኮች ት/ቤቱንና ተማሪዎችን ለመደገፍ ውሳኔ ላይ ተደረሰ።
- ከፍተኛ ውጤት የሚያስመዘግቡ ግን ደግሞ ከዝቅተኛ ገቢ ቤተሰብ የሚመጡ ተማሪዎችን የትምህርትና ተያያዥነት ያላቸው ወጫቸውን በመሸፈን በትምህርታቸው እንዲበረቱ ስኮላርሺፕ ማቋቋም፤
- የት/ቤቱን ቤተ–መጻህፍት በማጠናከር (ዲጂታል ላይበራሪ በማቋቋም)ተማሪዎችን በትምህርታቸው የተሻለ ተፎካካሪ ማድረግ፤
- ሴት ተማሪዎችን ያለባቸውን ማህበረሰባዊ ተጽዕኖ ለመቅረፍ የተለያዩ የሊደርሺፕ ስልጠናዎችንና ድጋፎችን ማድረግ ናቸው።
ከነዚህ ውስጥ በቅድሚያ በመጀመሪያ ልንሰራው ያሰብነው ስኮላርሺፕ ማቋቋምና ቢያንስ 24 ተማሪዎችን በየዓመቱ የገንዘብና የማቴሪያል ድጋፍ ማድረግ እንዲሆን ተወስኖ ይህንንም ለማሳካት የገንዘብ ማሰባሰብ ስራ ከሰኔ 21 2009ዓም ጀምሮ ሲሰራ ቆይቷል። ለስኮላርሺፑ ያስፈልጋል ከተባለው 12,000 የአሜሪካ ዶላር ውስጥ 80 የቀድሞ ተማሪዎችና ወዳጆች 9,200 ዶላር በማዋጣት የዕቅዳችንን 77% ማሳከት ተችሏል። በዕውነቱ ይህንን ዕቅድ ለማሳካት በኢትዮጵያና በተለያዩ የውጭ ሃገራት ያላችሁ የቀድሞ ተማሪዎችና የሃሳቡ ደጋፊዎች ያሳያችሁት መነሳሳት እጅግ የሚያስደስትና የሚያኮራ ነው። አዘጋጅ ኮሚቴውም ሰለቸኝ ደከመኝ ሳይል ይህንን ዕቅድ ወደ ተግባር ለመቀየር ሲደክም ቆይቷል።
አዘጋጅ ኮሚቴው በየሁለት ሳምንቱ (አንዳንዴም በየሳምንቱ) የስካይፒ ስብሰባ በመጥራት ማንኛውም የህብረቱ ኣባል እንዲሳተፍ በማድረግ አመርቂ ስራዎችን ሰርቷል። ከነዚህም ውስጥ፤
- የስኮላርሺፕ አሰጣጥ መመሪያ በማዛጋጀትና የህብረቱ አባላት በሙሉ እንዲወያዩበትና እንዲከልሱት በማድረግ ፤
- የህብረቱ የባህርዳር ተወካዮች ከት/ቤቱ መምህራንና ርዕሰ መምህር ጋር መመሪያውን እንዲወያዩበትና እንዲከልሱት በማድረግ፤ (https://tanahaikbdr.com/2017/07/29/tana-family-scholarship-tfs-guideline/)
- ህብረቱንና ስኮላርሺፕ ፕሮግራሙን ለማስተዋወቅ ሺዲዮዎችን በማዘጋጀት፤(https://www.youtube.com/watch?v=WVEhO7ySOgI )
- የህብረቱ እያንዳንዱን እንቅስቃሴና ክንውን በህብረቱ ድህረ–ገጽ ላይ እንዲሰፍር ተደርጎ በማህበራዊ ድህረ–ገጾች የቀድሞ ተማሪዎች እንዲያነቡት፤ እንዲከታተሉና ሃሳብ እንዲሰጡ በማድረግ፤
- ህብረቱ ህጋዊ ዕውቅና እንዲያገኝ በአሜሪካ እንዲመዘገብ በማድረግ (ኢትዮጵያ ውስጥ ለማስመዝገብ ዝግጅቶች እየተደረጉ ነው) –https://tanahaikbdr.com/forms-and-other-documents /
- የ 2010 ዓ ም የስኮላርሺፕ አሸናፊዎችን ለመምረጥ በት/ቤቱ መምህራንና ርዕሰ–መምህር የሚመራ ኮሚቴ በማዋቀር ተማሪዎች ማመልከቻ ቅጽ እንዲሞሉ በማድረግና
- የ 2010 ዓ ም ስኮላርሺፕ ለመስጠትና የመክፈቻ ፕሮግራሙንም በት/ቤቱ ውስጥ መስከረም 20 ላይ ለማዘጋጀት እንቅስቃሴ ማድረግ
- ለት/ቤቱ መምህራንና የቀድሞ መምህራን የምስጋና የዕራት ግብዣ ማዘጋጀት
በዋናነት ይጠቀሳሉ።
ይህ ሁሉ መሆን የቻለው እናንተ ባደረጋችሁት ከፍተኛ ተሳትፎ ነው። በተለይ ባህርዳር ላይ የህብረቱ ተወካይ ላቀ እንዳለው የግል ስራውን ሁሉ በመበደል ይህ እቅድ ከዳር እንዲደርስ የከፈለው መስዋዕትነት እጂግ የሚደንቅ ነው።
ከጐናችን በመቆም ላበረታታችሁን፤ ቃላችንን አምናችሁ ገንዛባችሁንና ጊዜአችሁን ሳትሳሱ ለደገፋችሁን የከበረ አክብሮታችን ይድረሳችሁ። ጣና ሃይቅ ት/ቤት ባትማሩም በሃሳባችን ተስማምታችሁ ድጋፍ ላደረጋችሁልን በሙሉ እጅግ በጣም እናመሰግናለን። ለቀና ተሳትፏችሁ እውቅና መስጠት ስላለብን በህብረቱ ስም የምስጋና ሰርተፊኬት በማዘጋጀት ላይ ነን። በት/ቤቱም ውስጥ ቀጣይነት ባለው መልኩ በየዓመቱ የሚደረገው አስተዋጽዖ እንደማስታወሻ በመዝገብ እንዲቀመጥ ጥረት እያደረግን ነው።
በቀጣይ ሪፖርታችን ላይ የተሸለሙ ተማሪዎችን ስም ዝርዝርና አጠቃላይ የኦዲት ሪፖርት ይዘን እንቀርባለን። ት/ቤቱንና ተማሪዎችን ለመደገፍ የሚሰሩ ሌሎች ስራዎንን ለመደገፍ ከእኛ ጋር እንደምትሰሩ በሙሉ ልባችን እንተማመናለን። ቀና ተሳትፏችሁን በቋሚነት ለመቀጠል በድረ ገፃችን ላይ የሚገኘውን የአባልነት ፎርም እንድትሞሉም እንጋብዛለን (https://tanahaikbdr.com/contacts/ )።
አጠቃላይ የህብረቱ የሒሣብ ሪፖርት (https://tanahaikbdr.com/balance/)
ከዚህ በታች አጠቃላይ የሂሳብ ሪፓርት ቀርቧል (June 28, 2017 to Sept 17, 2017)፤
አጠቃላይ ገቢ
1. በጎ-ፈንድ-ሚ ኣካውንት የተሰበሰበ = $9,200 የአሜርካ ዶላር (Donation list) receipt
- አሜሪካ በተከፈተ የህብረቱ አካውንት የገባ = $125.00 የአሜርካ ዶላር receipt
- ለንደን በተከፋተ የባንክ ሒሳብ የገባ = £350.00 ፓውንድ (~$474.39 USD*)
- ባህርዳር በተከፈተው የዳሸን የባንክ ሒሳብ የገባ = 5300.00 ETB ብር (~$225.94 USD*)
አጠቃላይ ድምር= $10,025.33 የአሜርካ ዶላር
አጠቃላይ ወጪ
- የጎ-ፈንድ-ሚ ኣካውንት የአገልግሎት ክፍያ = $751.38 receipt
- የህብረቱን ህጋዊነት በሜሪላንድ ለማግኝት የተከፋለ = $269.86 receipt
አጠቃላይ ድምር = $1,021.24 የአሜርካ ዶላር
ከወጪ ቀሪ ድምር $10,025.33 – $1021.24 = $9,004.09 የአሜርካ ዶላር
* በዛሬ ምንዛሬ መሰረት መስከረም 07,2010 ዓ.ም (September 17, 2017 11:30am EST)
በጋራ ዓላማችን እንደምናሳካ እርግጠኞች ነን!
ከአክብሮት ጋር እናመሰግናለን።
የህብረቱ አስተባባሪዎች
I’m happy for being a member of this big charity