Tana Family Scholarship Organizers Meeting in Bahir Dar
The TFS committee in Bahir Dar officially started the scholarship process. The meeting was held with former students, teachers and director of the school in Tana Haik Bahir Dar. It was very fruitful discussion.
We would like to share the meeting minute prepared by the organizers Lake Endalew and Mastewal Alemu. They also added their recommendation about the resource allocation and TFS winner selection . All TFS committee members have suggested a brief meeting on Saturday August 26,2017 to sync-up the recommendations with existing TFS guideline.
ቀን 14/12/2009 ዓ/ም
የጣና ሐይቅ ቤተሰብ ስኮላርሽፕ መመሪያ ላይ ተመርኩዞ የቀድሞ የጣና ሐይቅ ተማሪዎች ማህበር ባሰባሰበው መጠኑ 12ሺ ዶላር ብቃት ያላቸውን ተማሪዎች መርጦ ድጋፍ ለማድረግ ሲሆን ለጀመሪያው ዙር 24 ተማሪዎችን ባቋቋመው ኮሚቴ አማካኝነት መምረጥ ነው፡፡
እነዚህን ተማሪዎች ለመምረጥ በማህበሩ የተዘጋጀውን ስኮላርሽፕ መመሪያ መሠረት በማድረግ ነው፡፡
በወይይቱ ተገኙ አባላት ፡-
- ነብዩ እጅጉ …. ር/መምህር
- ላቀ እንዳለው…. የቀድሞ ተማሪ
- ማስተዋል አለሙ …. የቀድሞ ተማሪ
- ሰገነት ፈንቴ …. መምህር
- ልዑልሰገድ ድረስ …. መምህር
- ስሜነህ አምሳሉ …. መምህር
- ፈለቀ አብርሃ…. መምህር
አጀንዳ
በተዘጋጀው ለስኮላርሺፕ መመሪያ ላይ መወያየት
በእያንዳንዱ መስፈርት ላይ ቤቱ በስፋት ከተወያዬ በኋላ የሚከተሉትን መመልመያ መስፈርቶች ቢካተቱ የሚል አስተያየት አቅርቧል፡፡ ባወጣው መስፈርት መሠረትም 12 ወንዶች 12 ሴቶች በድምሩ 24 ተማሪዎች ይመረጣሉ፡፡የሚከተሉት ተማሪዎች ከ9-12 ያሉትን ያካትታል፡፡
የመመልመያ መስፈርት
- ለወንድ ተማሪዎች የቀን ተማሪዎች የሆኑና የቀድሞ ዓመት ዉጤታቸው 88% እና በላይ መሆን አለበት፡፡ – መመሪያው ላይ 85% ነው፡፡ ነገር ግን የሚሰጠው እድል በየግሬድ ሌቨሉ 6 ተማሪዎች ብቻ በመሆኑና ከዚህም ውስጥ ወንዶች 3 ስለሚሆኑ ከ90% በላይ ያሉ ብዙ ወንድ ተማሪዎች ስላላሉ ተወዳዳሪዎችን ለመቀነስ ሲባል በሚል ነው፡፡
- ለሴት ተማሪዎች 85% እና ከዛ በላይ (የቀድሞ ዓመት ውጤታቸው) የት/ቤቱ የቀን ተማሪ የሆኑ
- የ9ኛ ክፍል ተማሪዎች የሚመለከቱት በ1ኛው ወሰነ ትምህርት በሚገኙት ውጤት ላይ ተመስርቶ ሲሆን ከላይ የተጠቀሱት መነሻና መድረሻ ነጥቦች ከዚህም ላይ ያገለግላሉ፡፡ -9ኛ ክፍልን በተመለከተ ተማሪዎች ከተለያየ ቦታ የ8ኛ ክፍል ውጤት ይዘው ስለሚመጡ በውጤታቸው ለማወዳደር አስቸጋሪ ስለሆነ እስኮላሩ ሁለተኛው ወሰነ ትምህርት ላይ ቢጀምር የሚል ነው፡፡
- ስኮላርሽፑ የሚያገለግለው ለአንድ ዓመት ብቻ ሲሆን ከዚህም ተጠቃሚ የነበሩ ተማሪዎች በሚቀጥለው ዓመት እንደአዲስ ተወዳድረው ማሸነፍ ካልቻለ ተጠቃሚ አይሆኑም፡፡
- ስኮላርሽፑ በየወሩ ይሰጣል፡፡ ሁሉም አሸናፊ ተማሪዎች ከአንድ ባንክ ቡክ እንዲከፍቱ በማድረግ በየወሩ ለባንኩ ድብዳቤ በመጸፍ ለማህበሩ አካውንት ተቀናሽ እየሆነ ለተማሪዎች ወደ አካውንታቸው ይገባል ይህም ሁሌም እንዲበረታቱ ያደርጋቸዋል
- ስኮላርሽፑ በገንዘብና በማተሪያል መልክ ይሆናል፡፡ ስኮላርሽፑ የሚሰጠው ከ10ኛ-12ኛ ተማሪዎች ለ10 ወራት (ከመስከረም አስከ ሰኔ) ይሆናል፡፡ ለ9ኛ ክፍል ተማሪዎች ለ5ወር ይሆናል
- ክፍያው ከፍና ዝቅ ሊል ይችላል፡፡ መዋጮው በጨመረና በቀነሰ ቁጥር ማለት ነው፡፡
- ለእያንዳንዱ ተማሪ የሚሰጠው እርዳት ከ500 ብር ያላነሰ እንዲሆን
- ከ10 – 12 የሚገኙ ተማሪዎች ከሐምሌ 5 – 10 ማመልከት ይጠበቅባቸዋል፡፡
- የ9ኛ ክፍል ተማሪዎች ከየካቲት 5 – 15 ማመልከት ይጠበቅበታል፡፡
- ማመልቻው ለት/ቤቱ ርዕሰ መምህር ጽ/ቤት ይቀርባል፡፡
- የውድድሩ ውጤት ይፋ የሚሆነው ማመልከቻው ከገባ በኋላ ባሉት አምስት ተከታታይ ቀናት ሆናል፡፡
- የመልማይ ኮሚቴ አባላት ሶስት በአገር ውስጥ ያሉ የቀድሞ ተማሪዎች እና ሶስት መምህራን ያቅፋል የት/ቤቱን ርዕሰ መምህር ጨምሮ በውጭ የሚገኙ ተማሪዎች ኮሚቴ ሲስማማበትና ሲጸድቅ ወደ ስራ ይገባል
የሚከተሉት ተማሪዎች ጾታ ብዛትና በክፍል ደረጃ
9ኛ ክፍል ከፍተኛ ነጥብ ያስመዘገቡ 2 ወንድ 2 ሴት
10ኛ ክፍል ከፍተኛ ነጥብ ያስመዘገቡ 2 ወንድ 2 ሴት
11ኛ ክፍል ስፔሻል ነጥብ ያስመዘገቡ 3 ወንድና ሴት ከናቹራል ሳይንስ ተማሪዎች
11ኛ ክፍል ከፍተኛ ነጥብ ያስመዘገቡ 1 ወንድ/ሴት ከሶሻል ሳይንስ ይሆናል
12ኛ ክፍል ከፍተኛ ነጥብ ስመዘገቡ 3 ወንድና ሴት ከናቹራል ሳይንስ ተማሪዎች
12ኛ ክፍል ከፍተኛ ነጥብ ያስመዘጉ 1 ወንድ/ሴት ከሶሻል ሳይንስ ይሆናል
ቀሪዎቹ 8ተማሪዎችን በተመለከተ
- በመመሪው 12 ተማሪዎች በእጣ ይመረጣሉ የሚል ሲሆን ወደ 8 ቢሆን የሚል የውሳኔ ሀሳብ ቀርቧል፡፡ በተጨማሪም በእጣ መለየት የሚለውን ሀሳብ አብዛኞቹ መምህራን አልደገፉትም ስለሆነም የሚከተሉት ሌሎች አማራጮች ቢኖሩ ተብለዋለል
- በፍተና ቢለዩ የሚል ሲሆን ይህም ቢሆን ፈተናውን ማውጣት ማራባት መፈተን የመሳሰሉት ስራዎች ሊታሰብባቸው የሚከቡ ጉዳዮች ናቸው
- ስኮላርሽፑን መስፈርቱን አሟልተው ከሞሉ ተማሪዎች ውስጥ በጣም ችግረኛ የሆኑትን በሪኮሜንዴሽን፤በኢንተርቪው እና በመሳሰሉን ከየግሬድ ሌቪሉ ሁለት ተማሪዎችን ከ9-12 ባጠቃላይ 8 ተማሪዎችን ብንመርጥ የሚል ነው
- እኩል ነጥብ ሁለት ተማሪዎች ቢያገኙ አንዱ የአካል ጉዳቶች ቢሆን ቅድሚያ ይሰጠዋል፡፡
- በሌላ ስኮላርሽፕ ዕድል ያገነ ተማሪ በዚህ ስኮላርሽፕ መወዳደር አይችልም፡፡ ሲረዳበት የነበረውን ድርጅት ካልተወ በቀር
- በት/ቤት ደረጃ የሚቋቋመው የመልማይ ኮሚቴ ሶስት አባላትን ያቀፈ ሲሆን የሚመረጠውም በስታፍ ነው በማለት የውሳኔ ሀሳብ ቀርቧል፡፡
ከላይ የቀረቡት በዕለቱ ውይይት የቀረቡ ሲሆን ዋናውን በቨይበር የላኩ ሲሆን በዚህ ሰነድ ላይ በተወሰነ ማብራሪያ ጨምሬበታለሁ፡፡
ትኩረት የሚያስፈልጋቸው ነገሮች የግል አስተያየት ላቀ
- መመሪያው በደንብ መታየት፤ መዳበር እና በርካታ ዝርዝር ጉዳዮችን ማካተት ይኖርበታል
- ማህበሩ በሀገር ውስጥ እውቅና ማግኘት እና ህጋዊ ማድረግ ተገቢ ነው
- የማህበሩ ዶክመንቶች በቀጣይ እንዴት መቀመጥ እደሚኖርባቸው በዝርዝር መታየት ይኖርበታል
የባጀት ፍላጎት በተመለከተ የተሰራ ሰንጠረጅ
| ክፍል | የተማሪ ብዛት | ጾታ | ብር | ወራት | ድምር በኢ.ብር | |
| ወንድ ሴት | ||||||
| 9ኛ | 6 | 3 | 3 | 500 | 5 | 15,000.00 |
| 10ኛ | 6 | 3 | 3 | 500 | 10 | 30,000.00 |
| 11ኛ | 6 | 3 | 3 | 500 | 10 | 30,000.00 |
| 12ኛ | 6 | 3 | 3 | 500 | 10 | 30,000.00 |
| ጠ.ድምር | 24 | 12 | 12 | 35 | 105,000.00 | |
ተጨማሪ አስተያየት የግል
- አንዳን እጅግ የተቸገሩ ተማሪዎች ስላሉ ለነሱ ቢያንስ ለ10 ተማሪዎች የቤት ኪራይ በወር 300 ብር ድምር 3000.00 ብር
- ለሴት ተማሪዎች በየወሩ ቢያንስ ለ100 ተማሪዎች ለንጽህና መጠበቂያ እቃዎች መርዳት ቢቻል ድምር በግምት 20,000.00 ብር ይህ ገንዘብ ለ9ኛ ክፍል ለ10 ወራት ሊሰጥ የነበርው ስኮላር ወደ 5ወር ዚቅ ስላለ ከዚያ የሚገኘውን ወደ ዚህ እርዳታ ቢዞር
ቃለ ጉባዔ ተዘጋጀ በላቀ እንዳለ
Send your comment at tanagraduates@gmail.com
- Viber group: https://invite.viber.com/?g=MCNz2pNfI0Y5jZVgy9VPR-lzyhXdJD2G
- https://www.facebook.com/groups/325812767871551/
- https://www.gofundme.com/TanaScholarship
Tana Haik Alumni Network