የጣና ቤተሰብ ስኮላርሺፕ አሰጣጥ መመሪያ

በቀድሞ የጣና ሐይቅ ምሩቃን ህብረት የተዘጋጀ

2. መግቢያ

2.1 ጣና ሃይቅ አጠቃላይ ት/ቤት

2.1.1 ስለ ት/ቤቱ

የጣና ሃይቅ አጠቃላይ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት በ1958 ዓም በባህር ዳር ከተማ ተመሰረተ። ት/ቤቱ ላባህርዳርና ለአካባቢው ማህበረሰብ ብቸኛ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት በመሆን አገልግሏል። ት/ቤቱ የዕውቀት ጮራ በመፈንጠቅ ከግማሽ ምዕተ ዓመት በላይ ለአካባቢው ማህበረሰብ አገልግሎት ሰጥቷል። ከመቋቋሙ በፊት የፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ የተማሪዎች ማደሪያ በመሆን አገልግሎት ሰጥቷል። እስከ ቅርብ ጌዜ ድረስ ጣና ሃይቅ ት/ቤት በባህርዳር ከተማ ክሚገኙት ሁለት ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤቶች መካከል አንዱ ነው። ት/ቤቱ በአሁኑ ወቅት ከ9-12ኛ ክፍል ተማሪዎችን እየተቀበለ የኮሌጅ መሰናዶ ዝግጅት በማስተማር ላይ ይገኛል።

2.1.2 የት/ቤቱ ስነ ህዝብ (ዴሞግራፊ)

በአሁኑ ወቅት የጣና ሀይቅ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት 2710 ተማሪዎችን ተቀብሎ እያስተማረ ይገኛል። ከነዚህም ውስጥ 49.7% (1,348) ወንድ፤ የተቀሩት 50.3% (1,362) ደግሞ ሴቶች ናቸው።

2.2 የጣና ሀይቅ የቀድሞ ተማሪዎች ህብረት

የጣና ሀይቅ የቀድሞ ተማሪዎች ህብረት ጥቂት የጣና ሀይቅ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት የቀድሞ ተማሪዎችና ወዳጆችን በመሰባሰብ በ2004 ዓ.ም. ተቋቋመ።  ህብረቱ በዋነኝነት የጣና ሀይቅ ት/ቤትንና የት/ቤቱ ማህበረሰብን በተለያየ መንገድ ማገዝን ዓላማ ያደረገ ሲሆን በአሁኑ ወቅት በሃገር ውስጥ እንዲሁም በውጭ ሃገር የሚኖሩ በርካታ አባላት አሉት።

ህብረቱ ከተመሰረተ ጀምሮ ለት/ቤቱ ካደረጋቸው ድጋፎች መካከል የሚከተሉት በዋነኝነት ይጠቀሳሉ፤

  • ለየት/ቤቱ ቤተ-መጻህፍት ወንበሮችና ጠረጴዛዎችን ገዝቶ ማስረከብና የቤተ-መጻህፍቱን አቅም ማጠናከር
  • በየዓመቱ በትምህርታቸው ብልጫ ያመጡ ተማሪዎችን መሸለም
  • ለት/ቤቱ መምህራንና የቀድሞ መምህራን የምስጋና የዕራት ግብዣ ማዘጋጀት
  • የት/ቤቱ ቤተ-መጻህፍት በኢንተርኔት ማጠናከር
  • ለት/ቤቱ የመጻህፍት ድጋፍ መስጠት
  • የቀድሞ ተማሪዎች ለት/ቤቱ ማህበረሰብ አነቃቂ ንግግሮች በማድረግ ተማሪዎችን ለበለጠ ውጤት የማነቃቃት ስራ ይገኙበታል።

በአሁኑ ወቅት ደግሞ የጣና ሀይቅ ቤተሰብ የትምህርት ዕድል (ስኮላርሽፕ) በማቋቋም ጠንካራ ስራዎችን ለመስራት አቅዷል። የትምህርት ዕድሉ ተማሪዎችን የበለጠ በማገዝ በወጤታቸው ተፎካካሪ የሆኑ ዜጎችን ለመፍጠርና በሳይንስና ቴክኖሎጂ ወይም በቢዝነስና በተዛማጅ የትምህርት ዘርፎች አጉሊ ውጤት የሚያስመዘግቡ ወጣቶችን ለማፍራት ያለመ ነው።

3. አላማ

በጣና ሃይቅ የት/ቤት ውስጥ የተሻለ ውጤት ያመጡ ተማሪዎችን የትምህርት ቁሳቁስና የተለያዩ ድጋፎችን ማድረግ።

በባህር ዳር ከተማ የግል ትምህርት ቤቶች መበራከት ምክንያት በመንግስት ት/ቤት የሚማሩ ተማሪዎች በአብዛኛው ከአነስተኛ ገቢ ያላቸው ቤተሰብ የሚመጡ ሲሆኑ የጣና  ሃይቅ ተማሪዎችም ከነዚህ መካከል ናቸው።  ስለዚህ ተማሪዎች ለተለያዩ ችግሮች ተጋላጭ ናቸው።  ለምሳሌ፥ የቤት ክራይ፤ የትራንስፖርት ወጪ፤ የት/ቤት መሳሪያወች እጥረት፤ ይገኙበታል። ይህንን ግምት ውስት በማስገባት በዚህ አንጋፋ ት/ቤት ለሚማሩ 24 ተማሪወች የትምህርት ዕድል (ስኮላርሽፕ) በማዘጋጀት በትምህርታቸው እንዲተጉ ለማድረግ እንዲሁም ሌሎች ተማሪዎችም  ለበለጠ ውጤት አንዲበረታቱ የሚያደርግ አላማ አለው።

 

4. ሽልማት

4.1 የስኮላርሽፕ አሸናፊዎች

በአመት ውስጥ በጠቅላላው ከ9ኛ እስከ 12ኛ ክፍል የሚማሩ ተማሪዎች ከአያንዳንዱ ክፍል (Grade) ስድስት  ስድስት ተማሪዎች ተመርጠው በጠቅላላው 24 ተማሪዎች ስድስት ትጠቃሚ ይሆናሉ። ከየክፍሉ ከሚመረጡት 6ቱ መካከል 3 ተማሪዎች በአጠቃላይ በትምህርት ዓመቱ ከፍተኛ ነጥብ ያላቸው ይሆናሉ። ቀሪወቹ 12 ተማሪዎች በክፍል 5፥1 የተጠቀሰውን መስፈርት የሚያሟሉ ፣ በአስተባባሪ ኮሚቴው የተመረጡ ተማሪዎች ይሆናሉ።

በተጨማሪም የጣና ቤተሰብ ስኮላርሽፕ ለሴት ተማሪዎች ልዩ ትኩረት በመስጠት ለሴቶችን ተሳትፍ ለማሳደግ ይሰራል። ስለሆነም፦

  1. መስፈርት ለሚያሟሉ ሴት ተማሪዎች የስኮላርሽፑን ቁጥር መጨመር፤
  2. ከሚያገኙት ስኮላርሽፕ በተጨማሪ ተያያዥነት ያላቸውን ድጋፍ ማድረግ ለምሳሌ፣ የምክር አገልግሎት እና የማጠናከሪያ ትምህርት፤
  3. የገንዘብ ድጋፍ በማድረግ በጾታቸው ምክንያት የሚደርስባጨውን ማህበረሰባዊ ጫና ለመቀነስ ፣ የተለያዪ የንጽህና መጠበቂያ አቃዎችን በማቅረብና  አስፈላጊ ሆነው በሚገኙ ድጋፎችን ለማድረግ ይሰራል።

4.2 ስኮላርሽፑ የሚሰጥበት  ጊዜ

ስኮላርሽፑ የሚሰጠው ለአንድ የትምህርት ዓመት ሲሆን ድጋፉ የሚደረገው በገንዘብና በትምህርት መርጃ መሳሪያዋች ይሆናል። ይሁንና ለአስተዳደር ዓመች እንዲሆን በማሰብ የስኮላርሽፕ አሸናፊ ተማሪዎች የሚደረግላቸው ድጋፍ በዓመት ሁለት ጊዜ ይሆናል ።

4.3 ስኮላርሽፑ የሚሰጥበት መንገድ

የጣና ቤተሰብ ስኮላርሽፕ ድጋፉ የሚያደርገው በገንዘብና በትምህርት መርጃ መሳሪያዋች ይሆናል። ነገር ግን የሚሰጠው የድጋፉ መጠን የሚወሰነው በሚገኘው የመዋጮ ገንዘብና እንደ ተማሪው  የሚያስፈልገው የእርዳታ ዓይነት ሊለያይ ይችላል ።

በተጨማሪም እርዳታ የሚሰጥበት ዓይነትና መጠን  የጣና ቤተሰብ ስኮላርሽፕ አባላት ሃሳብ ቀርቦበት ከጸደቀ በኋላ ተፈፃሚ ይሆናል ።

5. የትምህርት ዕድል (ስኮላርሽፕ) ማመልከቻ

5.1 መስፈርት

ሁሉም የጣና ሀይቅ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት በመማር ላይ ያሉ ከ9-12 ክፍል ተማሪዎች ለዚህ የትምህርት ዕድል ማመልከት ይችላሉ። አመልካቾች የሚከተሉትን መስፈርቶች ማሟለት ይጠበቅባቸዋል፤

  • አመልካቾች በመማር ላይ ያሉ ከ9-12 ክፍል የቀን ተማሪዎች መሆን አለባቸው፤
  • አመልካች ተማሪዎች የቀድሞ አመት ውጤታቸው ከ85% በላይ አማካይ መሆን አለበት።

5.2 መሟላት ያለባቸው የማመልከቻ ዶክሜንት

ማንኛውም አመልካች ተማሪ የሚከተሉትን ዶክሜንቶች ማሟላት ይጠበቅበታል፤

  • የት/ቤት የተማሪ መታወቂያ ኮፒ
  • የተማሪው የቀድሞው ዓመት የትምህርት መረጃ (ትራንስክርቢት)ኮፒ
  • የተሞላ የትምህርት ዕድል ማመልከቻ ፎርም

የአመልካች ተማሪዎች የቤተሰብ መረጃ በማመልከቻ ፎርሙ ላይ የሚሰፍርበት ምክንያት መረጃው ለውስጥ አገልግሎት ለመጠቀም ብቻ ነው። ቤተሰብ መረጃ እንደ መስፈርት አያገለግልም።

5.3. ማመልከቻ ማቅረቢያ እና መጠናቀቂያ ጊዜ

በየዓመቱ የትምህርት ዓመቱ ከማለቁ በፊት ተማሪዎች የስኮላርሽፕ ማመልከቻ ፎርም ሞልተው የሚያቀርቡበት ቀናት በግልጽ በጣና ሀይቅ የቀድሞ ተማሪዎች ህብረት አማከኝነት በማስታወቂያ ይፋ ይደረጋል። ማስታወቂያውም የማመልከቻ መስፈርቱን እንዲሁም የማመልከቻ ቦታና ቀን በግልጽ የሚያሳይ ይሆናል።

5.4.ማመልከቻ ማስረከቢያ

አመልካች ተማሪዎች ማመልከቻቸውን በባሀርዳር ከተማ የማህበሩ ተወካዮች ማስገባት ይችላሉ።

6.  የስኮላርሽፕ  አሰተዳደር እና  መዋቅር

6.1 የስኮላርሽፕ አሰተዳደር ኮሚቴ

የጣና ቤተሰብ ስኮላርሽፕ አሰተዳደር ኮሚቴ በየዓመቱ በሚከሄድ ጠቅላላ ጉባዔ ይመረጣል። የስኮላርሽፕ አሰተዳደር ኮሚቴው የሚከተሉትን አባላት የያዘ ሆናል፤

  • ሶሰት በባህርዳር የሚኖሩ የቀድሞ ተማሪዎች ተወካዮች፤
  • አምስት በውጭ ሃገር  የሚኖሩ የቀድሞ ተማሪዎች ተወካዮች፤
  • ሁለት የትምህርት ቤቱ አስተማሪዎች (አስተዳደር ሰራተኞች)ን የያዘ ይሆናል።

6.2 የአስተዳደር ኮሚቴው ሃላፊነት

  • የአመልካች ተማሪዎችን መርሃግብር ማውጣት እና ማሳወቅ፤
  • ማመልከቻዎችን ማሰባሰብ እና ማስተባበር፤
  • ማመልከቻዎችን ማጣራት እና ወጤት ማሳወቅ፤
  • የተማሪዎችን ውጤት ማመሳከርና ከአስተማሪዎች ወይም ከት/ቤት አስተዳደረ ጋር ግምገማዎችን መቀበል፤
  • የውጤት መግለጫ ጊዜውን በአመት አንድ መወሰን ጊዜ መወሰን፤
  • የአመቱን የሽልማት በጀት ማቀድና ለህብረቱ በጀት መወሰን፤
  • በአመት ሁለት ግዜ ሪፖርት ማሳወቅ እና እቅዶችን ነድፎ በጠቅላላ ጉባኤው ማስፀደቅ፤
  • ሽልማቱ በአመት ሁለት ጊዜ እንዲሰጥ ማድረግ፤
  • የአመቱን የብቃት መመዛኛ ሪፖርት ማዛጋጀትና ለህብረቱ እንዲሁም ለት/ቤቱ አስተዳደር ማቅረብ። ሪፓርቱ የገንዘብና የአፈጻጻም ሁኔታዎቹን የሚያካትት ሲሆን የወደፊት እርማቶቹን  የያዘ ሊሆን ይገባል።

የስኮላሽፕ ኮሚቴ ለተሸላሚዎች ሽልማቱን የሚሰጥበትን መንገድ እንደአመቺነቱ ሊተገብረው ይችላል። የገንዘብ ሽልማቱ በአመት ሁለት ጊዜ በአሸናፊዎች የባንክ ሂሳባቸው ውስጥ ገቢ ይሆናል። ቢቻል የመንፈቀ አመቱ ትምህርት ከመጀመሩ ከሁለት እስከ አራት ሳምንት ቀድሞ ይሰጣል።

7. የግምገማ ሂደት

የአስተዳደር ኮሚቴው ንዑስ ክፍል 5.1ን መሰረት በማድረግ የተላኩ ማመልከቻዎችን ይገመግማል ፤ ስብሰባ በመጥራትም በማጣሪያው ያለፉ ተማሪዎችን  ዝርዝር ያዘጋጃል።

8. የዕጣና ማስታዎቂያ ሂደት

ኮሚቴው የመጨረሻ አሸናፊዎችን ለመለየትና ይፋ ለማድረግ ልዩ ዝግጅት ያዘጋጃል። የመጨረሻ አሸናፊዎችን ለመለየት ሁሉም እጩ ተወዳዳሪዎች የክፍል ደረጃቸውንና ጾታቸውን ግምት ውስጥ ባስገባ መልኩ ወደ እጣ እንዲገቡ ይደረጋል። ጥሪ በተደረገላቸው እንግዶች አማካኝነትም የእጣ ማውጣት ሂደቱ ይካሄድ እና አሸናፊዎች እንዲታዎቁ ይደረጋል። በመጨረሻም ኮሚቴው የእጣ ውጤቱን መሰረት በማድረግ የመጨረሻ 24 አሸናፊዎችን ስም ዝርዝር ይፋ ያደርጋል።

9. የገቢ ማሰባሰቢያ መንገድ

የጣና ሐይቅ የቀድሞ ተማሪዎች ህብረት በአሁኑ ሰዓት ዋና የገቢ ምንጮቹ ከቀድሞ የት/ቤቱ ተማሪዎችና የት/ቤቱ ወዳጆች በሚገኝ ድጋፍ ሲሆን ይህንን መርሃ ግብር ለማስቀጠል ልዩ ልዩ የገቢ ማሰባሰቢያ መንገዶችን ያመቻቻል። ለዚህ ዓመት በእቅድ ላይ የተያዘዉን ነጻ የትምህርት እድል መርሃ ግብር ለማስቀጠል 12,000 የአሜሪካን ዶላር በጀት የተያዘ ሲሆን መርሃ ግብሩን ዳር ለማድረስ ህብረቱ ልዩ ልዩ የገንዘብ ማሰባሰቢያ መንገዶችን መተግበርና የተለያዩ አካላትንም ማሳተፍ እንደሚገባ ያምናል። ከተለያዩ የውጭ አካላት ሊገኝ የሚችለውን ድጋፍ ለማፋጠን የጣና ሐይቅ የቀድሞ ተማሪዎች ህብረት በአሜሪካን ሃገር እንደ ተራድዖ ድርጅት ህጋዊ እውቅናን በማግኘት ተመዝግቧል።

10. ቁጥጥርና መዝገብ አያያዝ

ነጻ የትምህርት እድሉን የተመለከተ ማንኛውም ወጪ በውጭ ኦዲተር የሚፈተሽ ሲሆን ውጤቱም ሁሉም አባላት እንዲያዩት ይደረጋል።

Join Tana Haik Alumni Network :

Tana Haik Alumni Network

Tana Family Scholarship Organizers Meeting in Bahir Dar

 Tana Family Scholarship Organizers Meeting in Bahir Dar   

The TFS committee in Bahir Dar officially started the scholarship process. The meeting was held with former students, teachers and director of the school in Tana Haik Bahir Dar. It was very fruitful discussion.

We would like to share the meeting minute prepared by the organizers Lake Endalew and Mastewal Alemu. They also added their recommendation about the resource allocation and TFS winner selection . All  TFS committee members have suggested a brief meeting on Saturday August 26,2017 to sync-up the recommendations with existing TFS guideline.   

Please find well written report below.
Thank you Lake and Mastewal

                                                                               

                                                                                                           ቀን 14/12/2009 ዓ/ም

የጣና ሐይቅ ቤተሰብ ስኮላርሽፕ መመሪያ ላይ ተመርኩዞ የቀድሞ የጣና ሐይቅ ተማሪዎች ማህበር ባሰባሰበው መጠኑ 12ሺ ዶላር ብቃት ያላቸውን ተማሪዎች መርጦ ድጋፍ ለማድረግ ሲሆን ለጀመሪያው ዙር 24 ተማሪዎችን ባቋቋመው ኮሚቴ አማካኝነት መምረጥ ነው፡፡

እነዚህን ተማሪዎች ለመምረጥ በማህበሩ የተዘጋጀውን ስኮላርሽፕ መመሪያ መሠረት በማድረግ ነው፡፡

በወይይቱ ተገኙ አባላት ፡-

  1. ነብዩ እጅጉ …. ር/መምህር
  2. ላቀ እንዳለው…. የቀድሞ ተማሪ
  3. ማስተዋል አለሙ …. የቀድሞ ተማሪ
  4. ሰገነት ፈንቴ …. መምህር
  5. ልዑልሰገድ ድረስ …. መምህር
  6. ስሜነህ አምሳሉ …. መምህር
  7. ፈለቀ አብርሃ…. መምህር

  አጀንዳ

በተዘጋጀው ለስኮላርሺፕ መመሪያ ላይ መወያየት

በእያንዳንዱ መስፈርት ላይ ቤቱ በስፋት ከተወያዬ በኋላ የሚከተሉትን መመልመያ መስፈርቶች ቢካተቱ የሚል አስተያየት አቅርቧል፡፡ ባወጣው መስፈርት መሠረትም 12 ወንዶች 12 ሴቶች በድምሩ 24 ተማሪዎች ይመረጣሉ፡፡የሚከተሉት ተማሪዎች ከ9-12 ያሉትን ያካትታል፡፡

                      የመመልመያ መስፈርት

  • ለወንድ ተማሪዎች የቀን ተማሪዎች የሆኑና የቀድሞ ዓመት ዉጤታቸው 88% እና በላይ መሆን አለበት፡፡ – መመሪያው ላይ 85% ነው፡፡ ነገር ግን የሚሰጠው እድል በየግሬድ ሌቨሉ 6 ተማሪዎች ብቻ በመሆኑና ከዚህም ውስጥ ወንዶች 3 ስለሚሆኑ ከ90% በላይ ያሉ ብዙ ወንድ ተማሪዎች ስላላሉ ተወዳዳሪዎችን ለመቀነስ ሲባል በሚል ነው፡፡
  • ለሴት ተማሪዎች 85% እና ከዛ በላይ (የቀድሞ ዓመት ውጤታቸው) የት/ቤቱ የቀን ተማሪ የሆኑ
  • የ9ኛ ክፍል ተማሪዎች የሚመለከቱት በ1ኛው ወሰነ ትምህርት በሚገኙት ውጤት ላይ ተመስርቶ ሲሆን ከላይ የተጠቀሱት መነሻና መድረሻ ነጥቦች ከዚህም ላይ ያገለግላሉ፡፡ -9ኛ ክፍልን በተመለከተ ተማሪዎች ከተለያየ ቦታ የ8ኛ ክፍል ውጤት ይዘው ስለሚመጡ በውጤታቸው ለማወዳደር አስቸጋሪ ስለሆነ እስኮላሩ ሁለተኛው ወሰነ ትምህርት ላይ ቢጀምር የሚል ነው፡፡
  • ስኮላርሽፑ የሚያገለግለው ለአንድ ዓመት ብቻ ሲሆን ከዚህም ተጠቃሚ የነበሩ ተማሪዎች በሚቀጥለው ዓመት እንደአዲስ ተወዳድረው ማሸነፍ ካልቻለ ተጠቃሚ አይሆኑም፡፡
  • ስኮላርሽፑ በየወሩ ይሰጣል፡፡ ሁሉም አሸናፊ ተማሪዎች ከአንድ ባንክ ቡክ እንዲከፍቱ በማድረግ በየወሩ ለባንኩ ድብዳቤ በመጸፍ ለማህበሩ አካውንት ተቀናሽ እየሆነ ለተማሪዎች ወደ አካውንታቸው ይገባል ይህም ሁሌም እንዲበረታቱ ያደርጋቸዋል
  • ስኮላርሽፑ በገንዘብና በማተሪያል መልክ ይሆናል፡፡ ስኮላርሽፑ የሚሰጠው ከ10ኛ-12ኛ ተማሪዎች ለ10 ወራት (ከመስከረም አስከ ሰኔ) ይሆናል፡፡ ለ9ኛ ክፍል ተማሪዎች ለ5ወር ይሆናል
  • ክፍያው ከፍና ዝቅ ሊል ይችላል፡፡ መዋጮው በጨመረና በቀነሰ ቁጥር ማለት ነው፡፡
  • ለእያንዳንዱ ተማሪ የሚሰጠው እርዳት ከ500 ብር ያላነሰ እንዲሆን
  • ከ10 – 12 የሚገኙ ተማሪዎች ከሐምሌ 5 – 10 ማመልከት ይጠበቅባቸዋል፡፡
  • የ9ኛ ክፍል ተማሪዎች ከየካቲት 5 – 15  ማመልከት ይጠበቅበታል፡፡
  • ማመልቻው ለት/ቤቱ ርዕሰ መምህር ጽ/ቤት ይቀርባል፡፡
  • የውድድሩ ውጤት ይፋ የሚሆነው ማመልከቻው ከገባ በኋላ ባሉት አምስት ተከታታይ ቀናት ሆናል፡፡
  • የመልማይ ኮሚቴ አባላት ሶስት በአገር ውስጥ ያሉ የቀድሞ ተማሪዎች እና ሶስት መምህራን ያቅፋል የት/ቤቱን ርዕሰ መምህር ጨምሮ በውጭ የሚገኙ ተማሪዎች ኮሚቴ ሲስማማበትና ሲጸድቅ ወደ ስራ ይገባል

የሚከተሉት ተማሪዎች ጾታ ብዛትና በክፍል ደረጃ

9ኛ ክፍል ከፍተኛ ነጥብ ያስመዘገቡ 2 ወንድ 2 ሴት

10ኛ ክፍል ከፍተኛ ነጥብ ያስመዘገቡ 2 ወንድ 2 ሴት

11ኛ ክፍል ስፔሻል ነጥብ ያስመዘገቡ 3 ወንድና ሴት ከናቹራል ሳይንስ ተማሪዎች

11ኛ ክፍል ከፍተኛ ነጥብ ያስመዘገቡ 1 ወንድ/ሴት ከሶሻል ሳይንስ ይሆናል

12ኛ ክፍል ከፍተኛ ነጥብ ስመዘገቡ 3 ወንድና ሴት ከናቹራል ሳይንስ ተማሪዎች

12ኛ ክፍል ከፍተኛ ነጥብ ያስመዘጉ 1 ወንድ/ሴት ከሶሻል ሳይንስ ይሆናል  

ቀሪዎቹ 8ተማሪዎችን በተመለከተ

  • በመመሪው 12 ተማሪዎች በእጣ ይመረጣሉ የሚል ሲሆን ወደ 8 ቢሆን የሚል የውሳኔ ሀሳብ ቀርቧል፡፡ በተጨማሪም በእጣ መለየት የሚለውን ሀሳብ አብዛኞቹ መምህራን አልደገፉትም ስለሆነም የሚከተሉት ሌሎች አማራጮች ቢኖሩ ተብለዋለል
  • በፍተና ቢለዩ የሚል ሲሆን ይህም ቢሆን ፈተናውን ማውጣት ማራባት መፈተን የመሳሰሉት ስራዎች ሊታሰብባቸው የሚከቡ ጉዳዮች ናቸው
  • ስኮላርሽፑን መስፈርቱን አሟልተው ከሞሉ ተማሪዎች ውስጥ በጣም ችግረኛ የሆኑትን በሪኮሜንዴሽን፤በኢንተርቪው እና በመሳሰሉን ከየግሬድ ሌቪሉ ሁለት ተማሪዎችን ከ9-12 ባጠቃላይ 8 ተማሪዎችን ብንመርጥ የሚል ነው
  • እኩል ነጥብ ሁለት ተማሪዎች ቢያገኙ አንዱ የአካል ጉዳቶች ቢሆን ቅድሚያ ይሰጠዋል፡፡
  • በሌላ ስኮላርሽፕ ዕድል ያገነ ተማሪ በዚህ ስኮላርሽፕ መወዳደር አይችልም፡፡ ሲረዳበት የነበረውን ድርጅት ካልተወ በቀር  
  • በት/ቤት ደረጃ የሚቋቋመው የመልማይ ኮሚቴ ሶስት አባላትን ያቀፈ ሲሆን የሚመረጠውም በስታፍ ነው በማለት የውሳኔ ሀሳብ ቀርቧል፡፡

ከላይ የቀረቡት በዕለቱ ውይይት የቀረቡ ሲሆን ዋናውን በቨይበር የላኩ ሲሆን በዚህ ሰነድ ላይ በተወሰነ ማብራሪያ ጨምሬበታለሁ፡፡

ትኩረት የሚያስፈልጋቸው ነገሮች የግል አስተያየት ላቀ

  • መመሪያው በደንብ መታየት፤ መዳበር እና በርካታ ዝርዝር ጉዳዮችን ማካተት ይኖርበታል
  • ማህበሩ በሀገር ውስጥ እውቅና ማግኘት እና ህጋዊ ማድረግ ተገቢ ነው
  • የማህበሩ ዶክመንቶች በቀጣይ እንዴት መቀመጥ እደሚኖርባቸው በዝርዝር መታየት ይኖርበታል

የባጀት ፍላጎት በተመለከተ የተሰራ ሰንጠረጅ

ክፍል የተማሪ ብዛት ጾታ ብር ወራት ድምር በኢ.ብር
ወንድ         ሴት
9ኛ 6 3 3 500 5 15,000.00
10ኛ 6 3 3 500 10 30,000.00
11ኛ 6 3 3 500 10 30,000.00
12ኛ 6 3 3 500 10 30,000.00
ጠ.ድምር 24 12 12 35 105,000.00

ተጨማሪ አስተያየት የግል

  • አንዳን እጅግ የተቸገሩ ተማሪዎች ስላሉ ለነሱ ቢያንስ ለ10 ተማሪዎች የቤት ኪራይ በወር 300 ብር ድምር 3000.00 ብር
  • ለሴት ተማሪዎች በየወሩ ቢያንስ ለ100 ተማሪዎች ለንጽህና መጠበቂያ እቃዎች መርዳት ቢቻል ድምር በግምት 20,000.00 ብር ይህ ገንዘብ ለ9ኛ ክፍል ለ10 ወራት ሊሰጥ የነበርው ስኮላር ወደ 5ወር ዚቅ ስላለ ከዚያ የሚገኘውን ወደ ዚህ እርዳታ ቢዞር

         ቃለ ጉባዔ ተዘጋጀ በላቀ እንዳለ

Send your comment at tanagraduates@gmail.com

Tana Haik Alumni Network