ዜና – News Update

የ94 ባች 10ኛ ዓመት ምረቃ በዓላቸውን ለማክበር በዝግጅት ላይ ናቸው።

በዓሉን አስመልክቶ ሊሠሩ ከታሰቡት መካከል 80 ወንበሮችንና ተጨማሪ መጽሐፍትን ለላይብረሪው ማቅረብ፣ ለንባብም ዝግጁ እንዲሆን ማድረግ ይገኝበታል (ለበለጠ መረጃ ዝርዝር ዕቅዱን /Draft action plan/ ይመልከቱ)፤ ዕቅዱን ለማየት የቀረበውን ሊንክ ከተከተሉ በኋላ download from sendspace የሚለውን አማራጭ ይከተሉ።


ለመጪው ቅዳሜ (መጋቢት 29/Apr.7) የገቢ ማሰባሰቢያ እራት ፕሮግራም ከቀድሞ መምህራን ጋር፣
እሁድ (መጋቢት 30/Apr 8) ት.ቤቱን በህብረት ከሁሉም የት.ቤቱ አካላት ጋር የማፅዳት ፕሮግራም 
ቅዳሜ (ሚያዚያ 6/Apr 14) 10ኛ ዓመት በዓሉን በት.ቤቱ ላይብረሪ የማክበር ዕቅድ ተይዟል።
ለእራት ፕሮግራሙ አስተባባሪ ኮሚቴው እንዲካፈሉ ከጋበዛቸው መምህራን ሌላ ‘መምህር እከሌን እኔ እራት መጋበዝ እፈልጋለሁ’ ብሎ ማሳወቅ ይቻላል (የተወካዮቹ አድራሻ ዕቅዱ ላይ አለ)። በዝግጅቱ ላይ አፋጣኝ መፍትሔ ለሚያስፈልጋቸው ችግሮች የሚሆን የገቢ ማሰባሰብ (Fund raising) ይካሄዳል።
የእራት ዝግጅቱን በቀጥታ በዚህ ብሎግ የመዘገብ ዕቅድ ተይዟል። እንዳያመልጠን!

1 thought on “ዜና – News Update

comment